Fana: At a Speed of Life!

የሚኒስትሮች ምክር ቤት የ6 ወራት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ አካሄደ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 15፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የሚያካሂደውንና በዓመታዊ ዕቅድ መሠረት የተካሄደውን የግማሸ ዓመት ብሔራዊ የሥራ ክንውን ምዘና መርተዋል።

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ምዘና የተካሄደው 2013 ዓ.ም. መጋመሱን ተከትሎ መሆኑን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጸደቀው ዓመታዊ ዕቅድ መሠረት ቀጣይነት ያለውን ምዘና መካሄዱ ክፍተቶችን በመሙላት እና አስፈጻሚ አካላት ተጠያቂ እንዲሆኑ ያደርጋል ብለዋል፡፡

እንዲሁም ለዜጎች ተገቢው አገልግሎት መቅረቡን ለማረጋገጥ እንደሚያስችልም በፌስቡክ ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

በስራ ምዘናው ሁሉም የካቢኔ አባላት የተሳተፉ ሲሆን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶቹ በዕቅድ ዘመኑ ያሳኳቸውን ተግባራትና ያጋጠሟቸውን ተግዳሮች በዝርዝር አቅርበዋል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.