Fana: At a Speed of Life!

የሚኒስትሮች ኮሚቴ የዕለት ደራሽ ድጋፍን ከማሳለጥ በተጨማሪ የተፈናቀሉ ወገኖችን መልሶ የማቋቋምና መሰረተ ልማትን ወደነበረበት የመመለስ ርብርብ መቀጠሉን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥር 9፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የብሄራዊ አስቸኳይ ጊዜ አስተባባሪ ማዕከል ዘርፈ ብዙ ምላሽ ሰጪ የሚኒስትሮች ኮሚቴ የዕለት ደራሽ ድጋፍን ከማሳለጥ በተጨማሪ በየአካባቢው የተፈናቀሉ ወገኖችን መልሶ የማቋቋምና መሰረተ ልማትን ወደነበረበት የመመለስ ርብርብ መቀጠሉን ገለጸ።
ኮሚቴው በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል የተካሄደውን የህግ ማስከበር ዘመቻ ተከትሎ ሰብዓዊና ማህበራዊ ቀውሶች ምላሽ አሰጣጥ እና መልሶ የማቋቋም ሂደት ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን አስታውቋል።
የሚኒስትሮች ኮሚቴው በየጊዜው አስቸኳይ ፍላጎቶችን ደረጃ በደረጃ በመለየት፣ አፈጻጸማቸውን በመከታተል፣ አቅጣጫ በመስጠትና ውሳኔዎችን በማስተላለፍ በየአካባቢው ከተቋቋሙ የአስቸኳይ ጊዜ ተግባራት ፈጻሚ ማዕከላትን ተግባራት ለመከታተል በመደበኛነት በየሁለት ቀናት ይገናኛል።
በዚህም የሚኒስትሮች ኮሚቴው መደበኛ ስብሰባውን በሰላም ሚኒሰትር ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ሰብሳቢነት አካሂዷል።
እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት የየዘርፍ አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ በቀጣይ ቅድሚያ የሚሰጣቸው ጉዳዮች ተለይተው አቅጣጫ መሰጠቱን ከሰላም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.