Fana: At a Speed of Life!

የማህበራዊ ችግር ተጎጂዎች ማገገሚያና ልማት ማዕከል ተመረቀ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 25፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)በአዲስ አበባ ከተማ የተሰራው የማህበራዊ ችግር ተጎጂዎች ማገገሚያና ልማት ማዕከል ህንጻ ተመረቀ።

በማዕከሉ የምርቃ ሥነ ሥርዓት የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ የማህበረሰቡን ችግር ማቃለል የከተማ አስተዳደሩ እቅድ ነው ብለዋል።

በከተማ አስተዳደሩ ችግር ፈቺ ስራዎችን እየሰራን ነው ያሉት ምክትል ከንቲባዋ ማዕከሉ የጎደሉትን እያሟላን የዜጎችን ህይወት መታደጋችንን እንቀጥላለን ብለዋል።

የማዕከሉ ግንባታ ሁለት ዓመታትን የፈጀ ሲሆን፥ ከ75 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ እንደተደረገበት ተገልጿል።

ማዕከሉ 32 ክፍሎች ሲኖሩት፥ 1ሺህ ሰዎች የማስተናድ አቅም አለውም ተብሏል።

በዚህ ማዕከል የጎዳና ላይ ተዳዳሪዎች፣ አካል ጉዳተኞች እና የማህበራዊ ችግር ተጋላጮች ገብተው የሕይወት እና ስራ ክህሎት ሥልጠናዎችን እንዲያገኙ ያስችላል መባሉን የዘገበው ኢቢሲ ነው።

በማዕከሉ ስልጠና የሚያገኙ ዜጎች ራሳቸውንም ሆነ ህብረተሰቡንም የሚጠቅሙ እንዲሆኑ የሚሰራ ማዕከል ስለመሆኑም ተገልጿል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.