Fana: At a Speed of Life!

የማዕድን ሚኒስቴር በአፋር ክልል ለተፈናቀሉ ወገኖች የ30 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 9፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የማዕድን ሚኒስቴር በአፋር ክልል በአሸባሪው የህወሓት ቡድን ለተፈናቀሉ ወገኖች የ30 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ።
ድጋፉ ለተፈናቀሉና ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች የሚውል ሲሆን÷ የማዕድን ሚኒስትር ኢንጂነር ታከለ ኡማ በሰመራ ከተማ ተገኝተው ለክልሉ ርእሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ አስረክበዋል።
ኢንጅነር ታከለ በአሁኑ ሰዓት ኢትዮጵያውያን በሁሉም መስክ የሽብር ቡድኑን እየተፍለሙ ይገኛሉ ፤ የአፋር ህዝብ እየፈፀመ ላለው ተጋድሎ ለሌሎቻችን አርአያ በመሆኑ ለማበረታታት ድጋፍን አድርገናል ብለዋል።
የኢትዮጵያ የልማት ጉዞ የሚደናቀፍ የሚመስላቸው በርካቶች አሉ ፈተናውን ለማለፍ የአፍፋር ህዝብ አንድነት ማሳያ ነው።
ድጋፉ በአፋር ክልል በማዕድን ዘርፍ ከተሰማሩ ኩባንያዎች እና ድርጅቶች የተሰበሰበ ነው ብለዋል።
የህወሃት የሽብር ቡድን የአፋር ህዝብ እና አርብቶ አደር የሚጠቀምባቸውን መሰረተ ልማቶች በማውደም ሰብዓዊ ቀወስ በማድረሱ ምክንያት በርካቶች ለችግር ተጋልጠዋል ያሉት ኢንጅነር ታከለ ወደፊትም ሌሎችን በማስተባበር ድጋፍን አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል።
የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ የሽብር ቡድኑ በአፋር እና በአማራ ክልል ሰርጎ በመግባት በአርሶ አደሩ እና አርብቶ አደሩ ላይ ከፍተኛ ጥፋት አድርሷል።
ትናንት ሃገር ሲመሩ የነበሩ የቀበሩትን የጦር መሳሪያ በማውጣት ህዝቡን በራሱ ሃብት እየወጉት ነው።
በአሁኑ ሰዓት የአፋር ህዝብ የሽብር ቡድኑን መውጫ መግቢያ በማሳጣት ዋጋ እያስከፈሉት ይገኛሉ።
በክልሉ እስካሁን ድረስ በተቋማት ብቻ 2 ነጥብ 5 ቢሊየን የሚገመት ንብረት በትግራይ ወራሪ ሃይሎች ተዘርፍል ብለዋል ።
የሰው ልጅ እንደ ዕቃ የተቆጠረበት የትግራይ ክልል ነው፤ ለዚህ ማሳያው የሽብር ቡድኑ ለውጊያ ያሰለፍቸው የትግራይ ወጣቶች በአፋር ምድር እንደ ቅጠል ረግፈዋል ያሉት አቶ አወል የጊዜ ጉዳይ ነው እንጅ ህወሃትን የሚያጠፍው ራሱ የትግራይ ህዝብ ነው።
አሁንም በሃሰት ትርክት በተቀነባበረ ድራማ የትግራይን ህዝብ በማታለል ”ሚሊን ተቆጣጠርነው ” ሰመራን ያዝነው” እያሉ ተጨማሪ ወጣቶችን እያስጨረሱ ይገኛል፣ አይደለም በመቆጣጠራቸው በማሰባቸው ብቻ ዋጋ እያስከፈላቸው እንደሚገኝ ተናግረዋል።
አሁንም የአፍር ህዝብ ከመከላከያ ሰራዊቱ ጎን በመሆን ታሪክ እየሰራ ነው፤ ወደፊትም ድጋፋችን በማጠናከር ኢትዮጵያን ከፍ እናደርጋለን። ”አፋር የኢትዮጵያ ምሽግ ናት” እናሸንፍለን ብለዋል።
ሁሉም ኢትዮጵያዊ ከመከላከያ ጋር ከተባበረ መከላከያ። ”የማይገፋ ዳሽን ተራራ ” ነው ያሉት አቶ አወል በችግር ላይ ለሚገኘው የአፋር ህዝብ እና አርብቶ አደር የማዕድን ሚንስቴር ላደረገው ድጋፍ በህዝቡ ስም እናመሰግናለን ብለዋል።
በምንይችል አዘዘው
ተጨማሪ መረጃ:- ከክልል መገናኛ ብዙሃን
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
+2
66,241
People reached
3,418
Engagements
Boost post
1.6K
28 Comments
32 Shares
Like

Comment
Share
+2
63,549
People reached
3,314
Engagements
Boost post
1.6K
27 Comments
32 Shares
Like

 

Comment
Share

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.