Fana: At a Speed of Life!

የማዕድን ሚኒስቴር ከክልል ቢሮዎች ጋር ያለፉትን 6 ወራት የዘርፉን አፈጻጸምን ገመገመ

አዲስ አበባ፣ ጥር 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የማዕድን ሚኒስቴር ከክልል የማዕድን ቢሮዎች ጋር ያለፉትን 6 ወራት የማዕድን ዘርፍ አፈጻጸምን ገመገመ።
የኢፌዴሪ የማዕድን ሚኒስትር ኢንጂነር ታከለ ኡማ በማህብራዊ ትስስር ገፃቸው እንዳመለከቱት፥ በግምገማው የተለያዩ ማዕድናት ጥቅም ላይ በማዋል ደረጃ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች የተዳሰሱ ሲሆን፥ በተለይም ከወርቅ ምርት ጋር በተያያዘ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች አበረታች ሆነው ተገኝተዋል።
በቀጣይ በተለይም ለባህላዊ የወርቅ አምራቾች ድጋፍ በማድረግ የወርቅ ምርትን ለመጨመር የሚያስችሉ ስራዎችን ለመስራት መግባባት ላይ መደረሱን ነው ሚኒስትሩ ያመለከቱት።
ለኢንዱስትሪ የሚቀርቡ ማእድናትን በተመለከተ በእንቅስቃሴ ወቅት በየአካባቢው ባሉ ኬላዎች እየገጠማቸው ያለውን ጊዜ የሚፈጅ አሰራር ክልሎች ማስተካከያ እንዲያደርጉም የጋራ መግባባት ላይ መደረሱንም ገልፀዋል።
በተጨማሪም በግጭት ውስጥ የቆየው የአማራ ክልል የማዕድን እንቅስቃሴ ወደ ስራ እንዲገባ በሙሉ አቅም እንቅስቃሴ እንደሚደረግ አስታውቀዋል።

 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.