Fana: At a Speed of Life!

የምሥራቅ አፍሪካ ማኅበረሰብ መሪዎች በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጉዳይ እየመከሩ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የምሥራቅ አፍሪካ ማኅበረሰብ መሪዎች በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና በአማፂያን መካከል ለተከሰተው ግጭት ዕልባት ለመሻት በኬንያ እየመከሩ መሆኑ ተገለጸ፡፡

የኬንያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ባዘጋጁት ስብሰባ ላይ የተገኙት በምሥራቅ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በተከሰተው ወቅታዊ የደኅንነት ሥጋት እና ሁኔታ ላይ ለመምከር መሆኑን ዘ ኢስት አፍሪካን ዘግቧል፡፡

በምክክሩ የኬንያ፣ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ ርዋንዳ፣ ቡሩንዲ እና ዩጋንዳ መሪዎች እየተሳተፉ ነው፡፡

ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ለአማፂያኑ ከለላ ሰጥተሻል በሚል ርዋንዳን እየወነጀለች ሲሆን ርዋንዳም በተደጋጋሚ ስታስተባብል መቆየቷን ኤ ኤፍ ፒ ዘግቧል፡፡

የኬንያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ÷ ሠላምን ለማስፈን ቀጠናዊ የምሥራቅ አፍሪካ ማኅበረሰብ ኃይል እንዲሰማራ ጥሪ አቅርበው ነበር፡፡

በጉዳዩ ላይ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የርዋንዳ ሠላም አስከባሪ ኃይል እንዲሳተፍ አልፈልግም ስትል አቤቱታዋን ማሰማቷም ተጠቁሟል።

ኬንያ እያስተናገደች የሚገኘው የምሥራቅ አፍሪካ ማኅበረሰብ ስብሰባ ÷የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ መንግስት እና አማፂያኑ ተቀራርበው የሚነጋገሩበትን ሁኔታ ያመቻቻል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.