Fana: At a Speed of Life!

የምሥራቅ አፍሪካ ማኅበረ-ሰብ አባል ሀገራት ከውጪ የሚገቡ ልባሽ ጨርቆችን እና ጫማዎችን ሊያግዱ መሆኑ ተነገረ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኬንያ፣ ዩጋንዳ፣ ታንዛኒያ፣ ሩዋንዳ እና ቡሩንዲ የልባሽ ጨርቆችንና ጫማዎችን ገቢ ንግድ ሊያግዱ መሆኑ ተነገሯል፡፡

ሀገራቱ በገቢ ንግድ ከውጭ የሚገቡ ልባሽ ጨርቆችንና ጫማዎችን የሚያግዱት የሀገር ውስጥ የጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪዎችን እና የጫማ ፋብሪካዎችን ለማበረታታት ነው ተብሏል፡፡

ከፈረንጆቹ 2016 ጀምሮም የሀገራቱ ዜጎች የሀገር ውስጥ ምርቶችን እንዲገዙ ሲወተወቱ መቆየታቸውን ዘ ኢስት አፍሪካ ዘግቧል፡፡

የምሥራቅ አፍሪካ ቢዝነስ ምክር ቤት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጆን ካሊሳ ፥ እንደ ሲንጋፖር እና ደቡብ ኮሪያ ያሉ የ”እስያ ነብሮች” የሚባሉ ሀገራት ያደጉት በሀገር ውስጥ ኢንዱስትሪዎቻቸው የሚመረቱ ምርቶች ከውጭ እንዳይገቡ ዕገዳ በመጣልና ለኢንዱስትሪዎቻቸው ከለላ በመሥጠት መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

የየትኛውም ሀገር ኢንዱስትሪዎች ከውጪ የሚገቡ ምርቶችን ሳያግዱ እና ከመንግስት ከለላ ሳይሰጣቸው አላደጉም ነው ያሉት ሥራ አስፈጻሚው፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.