Fana: At a Speed of Life!

የምርጫ ቅስቀሳ ሲያደርግ እጅ ከፍንጅ የተያዘ የተፎካካሪ ፓርቲ ታዛቢ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋለ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰሜን ሸዋ ዞን ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ በዛሬው ዕለት የምርጫ ቅስቀሳ ሲያደርግ እጅ ከፍንጅ የተያዘ የተፎካካሪ ፓርቲ ታዛቢ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋለ።
በወረዳው ጮሌ የምርጫ ክልል እናት ፓርቲን ወክሎ ታዛቢ የነበረው ዘበነ ለማ÷ ከጠዋቱ 3 ሰዓት ላይ መራጮች ወደ ምርጫ ጣቢያ በሚሄዱበት መንገድ ላይ እየጠበቀ ፓርቲውን ምርጡ እያለ ወረቀት ሲያድል እጅ ከፍንጅ ተይዟል፡፡
የወረዳው ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር አዳነ ጎሹ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት÷ ተጠርጣሪው ጥፋቱን ያመነ ሲሆን ምርመራው ተጣርቶ ክስ ሊመሰረት መሆኑን ገልጸዋል።
ተጠርጣሪው በምርጫ ዕለት የተከለከሉ ተግባራትን በመፈጸሙ በህግ ተጠያቂ ይሆናል ብለዋል።
የሰሜን ሸዋ ዞን ምርጫ ክልል አስተባባሪ አቶ ሙሉጌታ አክሊሉ ÷ድርጊቱ የሚወገዝ መሆኑን ገልጸው ፓርቲዎች ከእንዲህ አይነት ተመሳሳይ ተግባር እንዲቆጠቡም አሳስበዋል።
አላዩ ገረመው
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
May be an image of 1 person, standing and sky
0
People Reached
0
Engagements
Distribution Score
Boost Post
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.