Fana: At a Speed of Life!

የምስራቅ ሊቢያ መንግስት ስልጣን ለቀቀ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በካሊፋ ሃፍጣር ስር የሚገኘው የምስራቅ ሊቢያ መንግስት ከቤንጋዚ ተቃውሞ በኋላ ስልጣን መልቀቁ ተሰምቷል።

በጠቅላይ ሚኒስትር አብደላህ አልታኒ የሚመራው በምስራቅ ሊቢያ መንግስት በኑሮ ውድነት እና ሙስና ምክንያት በርካታ ተቃውሞዎች ከተነሱ በኋላ ስልጣኑን መልቀቁን ነው የተነገረው ፡፡

በሳምንቱ መጨረሻ በቤንጋዚ ከተማ የተገኙት ሰልፈኞች በካሊፋ ሃፍጣር መንግስት ስር የሚገኘው የምስራቅ ሊቢያ መንግስት ዋና መሥሪያ ቤት በእሳት ማቃጠላቸውም ተነግሯል።

በተጨማሪም ከካሊፋ ሃፍጣር የደህንነት ሃይሎች ጋር መጋጨታቸውም ነው የተነገረው፡፡

በሊቢያ ለረጅም ጊዜ በስልጣን የነበሩት ሙአመር ጋዳፊ በአውሮፓውያኑ 2011 በኔቶ ድጋፍ በሚያገኙ ኃይሎች ከስልጣን ተወግደው ከተገደሉ ወዲህ ሊቢያ ግጭት ውስጥ መሆኗ ይታወቃል።

የጄኔራል ከሊፋ ሃፍጣር ቃል አቀባይ ሰላማዊ ተቃውሞ የሚደገፍ ቢሆንም አሸባሪዎች እና የሙስሊም ወንድማማቾች ማዘዝ እንደማይችሉ ተናግረዋል።

ሊቢያ በአፍሪካ ትልቁ የነዳጅ እና ጋዝ ክምችት ያላት ሃገር ብትሆንም ለጄኔራል ሀፍጣር የሚሰራ ታጠቂ ቡድን ቁልፍ የነዳጅና ጋዝ ክምችት ስፍራዎችን በመዝጋት የኃይል መቆራረጥን በመፍጠር እና አገሪቱ በቢሊየን የሚቆጠር ዶላር ወደ ውጭ እንዳትልክ በማድረጉ ኪሳራ ውስጥ ገብታለች።

በሊቢያ በተቀናቃኝ መንግስታት መካከል የተኩስ አቁም ስምምነት ባለፈው ወር ይፋ መሆኑ የሚታዎስ ነው ፡፡

ምንጭ፦ ቢ.ቢ.ሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.