Fana: At a Speed of Life!

የምስራቅ አፍሪካ አገራት የተሳተፉበት ወታደራዊ መረጃ ልውውጥ ፎረም በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ሚያዚያ 8፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሰባት የምስራቅ አፍሪካ አገራት እየተሳተፉበት የሚገኝ ወታደራዊ መረጃ ልውውጥ ፎረም በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

ፎረሙ በቀጠናው ያለውን የሰላም እና መረጋጋት መልካም አጋጣሚን እንዲሁ የጸጥታ ችግሮችን በመለየት የመረጃና የተሞክሮ መለዋወጥን ዓላማ ያደረገ ነው።

በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የኢፌዲሪ የመከላከያ ሰራዊት መረጃ መምሪያ ዋና ሃላፊ ሌተናል ጀነራል ብርሃኑ በቀለ፥ በአንድ አካባቢ ያለ መልካም አጋጣሚም ሆነ ስጋት ድንበር ተሸጋሪ በመሆኑ በመረጃ ልውውጥና ትብብር አስፈላጊ መሆኑን አንስተዋል።

ዛሬ የተጀመረውም ፎረም የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ደህንነታቸው የሚጠበቅበትን የጋራ ስምምነት ለመፍጠር ያለመ መሆኑን ነው የተናገሩት።

በምስራቅ አፍሪካ ሃገራት የሚንቀሳቀሱ በርካታ የሽብር ቡድኖች መኖራቸውን የጠቀሱት ሌተናል ጀነራሉ፥ የሽብር ቡድኖቹ የሚያደርሱትን ጥቃት በጋራ ለመከላከል የቅድመ መረጃ ትንተናና ዝግጅት ለማድረግ ከስምምነት ለመድረስ ያስችላልም ብለዋል።

ከዚህ ቀደም በተናጥል ከአንዳንድ ሃገራት ጋር ይሰራ የነበረውን የደህንነት ስራ በቅንጅት ከሁሉም የምስራቅ አፍሪካ ሃገራት ጋር ለመስራት የጋራ የስምምነት ሰነድ እንደሚፈራረሙም ይጠበቃል፡፡

ፎረሙ ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ቀናት ይቆያል።

በቆንጅት ዘውዴ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.