Fana: At a Speed of Life!

የምስራቅ አፍሪካ የጥበባትና ባህል ፌስቲቫል መካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የምስራቅ አፍሪካ የጥበባትና ባህል ፌስቲቫል በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ።

የባህል ፌስቲቫሉ አካል የሆነው የጎዳና ላይ ትርዒት በመስቀል አደባባይ እየተካሄደ ነው፡፡

“ጥበባትና ባህል ለቀጠናዊ ትስስር” በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ ባለው  የጥበባትና ባህል ፌስቲቫል ላይ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር አቶ ቀጀላ መርዳሳ፣የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር መስፍን ቸርነት ፣የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲን ጨምሮ የፌስቲቫሉ ታዳሚዎች እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች እንዲሁም ከተለያዩ አገራት የመጡ የባህል ቡድን ተወካዮች  እየተሳተፉ ነው፡፡

ፌስቲቫሉ እስከ ሰኔ 12 ቀን 2014 ዓ.ም የሚቆይ ሲሆን፥ የተለያዩ ሀገራት ዲፕሎማቶች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በአብርሃም ፈቀደና በፈቲያ አብደላ

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.