Fana: At a Speed of Life!

የምስራቅ አፍሪካ የጥበባትና ባህል ፌስቲቫል በቀጠናው ያለውን እምቅ የባህል ሀብት ለማስተዋወቅ እድል የሚሰጥ ነው – አምባሳደር ዲና ሙፍቲ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የምስራቅ አፍሪካ የጥበባትና ባህል ፌስቲቫል በቀጠናው ሀገራት ያለውን እምቅ የባህል ትውፊትና ቅርሶችን ለአለም ለማስተዋወቅ መልካም እድል የሚፈጥር መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተናገሩ።

ፌስቲቫሉ በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት ዛሬ በተለያዩ ዝግጅቶች ተጀምሯል።

በስነስርዓቱ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ፥ የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት እርስ በእርስ የተሳሰረ እምቅ ሀብት ያላቸው በመሆኑ ይህን ሀብት በትብብር ሊጠብቁና ሊያስተዋውቁ ይገባል ብለዋል።

የባህልና ስፖርት ሚኒስትር አቶ ቀጀላ መርዳሳ በበኩላቸው ፥ የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ህዝቦችን እርስ በእርስ የሚያይዙ የተለያዩ ባህሎችና የባህል መገለጫዎች ያሉ በመሆናቸው እነሱን ለላቀ ወዳጅነት ልንጠቀማቸው ይገባል ብለዋል።

በየሀገራቱ ያሉ ትውፊቶችም ቀጠነዊ ትስስርን ለማሳደግ አጋዥ በመሆናቸው መሰል ፌስቲቫሎችን ለወደፊትም አጠናክረን እናካሂዳለን ሲሉ ተናግረዋል።

የደቡብ ሱዳን የባህል ሙዚዬምና ቅርስ ሚኒስቴርን በመወከል የተገኙት ዎች ዌክ ወል በበኩላቸው ፥ ምስራቅ አፍሪካ የብዝሃ ባህልና ቋንቋ ማዕከል በመሆኑ በየጊዜው ተመሳሳይ መድረኮች እየተዘጋጁ ህዝቦችን እርስ በእርስ ማቀራረብ ያስፈልጋል ብለዋል።

የምስራቅ አፍሪካ የጥበባትና ባህል ፌስቲቫል ለቀጣይ አምስት ቀናት በተለያዩ ዝግጅቶች እንደሚቀጥል ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል ።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.