Fana: At a Speed of Life!

የምትዋጉት አሸባሪውን ብቻ ሳይሆን ጋላቢዎቻቸውን ጭምር ነው – ሌተናል ጀነራል ባጫ ደበሌ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የምትዋጉት አሸባሪውን ብቻ ሳይሆን ጋላቢዎቻቸውን ጭምር ነው ሲሉ የመከላከያ ሚኒስቴር የሰራዊት ግንባታ ስራዎች ዋና አስተባባሪ ሌተናል ጄነራል ባጫ ደበሌ ገለጹ፡፡
ሌተናል ጄነራል ባጫ ደበሌ በጭፍራ ግምባር ተገኝተው ለሰራዊት አባላት ንግግር አድርገዋል።
ባደረጉት ንግግርም የሰራዊት አባላቱ ጀግኖች እንደሆኑ በመግለፅ፥ “የምትዋጉት አሸባሪውን ብቻ ሳይሆን ጋላቢዎቻቸውን ጭምር ነው” ብለዋል ።
የውስጥ ሀይሎች ለውጪ ወኪል ሆነው ኢትዮጵያን በሚወጉበት ወቅት በአንድነት ተነስተን አሸባሪዎችን ድባቅ እንመታለን ሲሉ አስገንዝበዋል ።
ይህ ትውልድ በዚህ ታሪካዊ ወቅት አሸባሪውን የመቅበር እድል በማግኘቱ ሊደሰት ይገባል ማለታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
የአፋር ክልል ርዕሰ መስተደድር አቶ አወል አርባ እና አትሌት ሻለቃ ሀይሌ ገብረስላሴ በስፍራው በመገኘት ሰራዊቱን አበረታተዋል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.