Fana: At a Speed of Life!

የምኅንድስና ዘርፍ ለቻይና ቀጣይ ዕድገት ቁልፍ ድርሻ እንዳለው ተመለከተ

አዲስ አበባ፣ጥቅምት 16፣2014 (ኤፍ ቢሲ) የምኅንድስና ትምህርት ዘርፍ ለቀጣይ የቻይና ቴክኖሎጂ እድገት ወሳኝ ሚና እንደሚጫወት ተገለጸ፡፡

በፈረንጆቹ ከጥቅምት 22 እስከ 24 በቻይና ፔኪንግ ዩኒቨርሲቲ በተካሄደው መድረክ ላይ የዩኒቨርሲቲው መማክርት ሊቀ መንበር ሹ ሻይፒንግ እንደተናገሩት ÷አዲሱ የምኅንድስና ትምህርት፣ ቀዳሚ የጥናት ስራዎች እና ወሳኝ ቴክኖሎጂዎች ለዩኒቨርሲቲው በማመንጨት ወሳኝ ድርሻ ይኖረዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው የተለያዩ ተሰጥዖዎችም መፍለቂያ ለመሆን ዕቅድ እንዳለው ነው ሊቀ መንበሩ የተናገሩት፡፡

በቻይና በተካሄደው ዓለም አቀፍ የምኅንድስና መድረክ ላይ ከ 200 በላይ ባለሥልጣናት፣ ምሁራን እና የኢንዱስትሪ ባለሙያዎች ተገኝተው የምኅንድስና ፕሮግራሞች ለማሳደግ ያለሙ በርካታ በክፍለ ጊዜዎች የተከፋፈሉ ውይይቶች ማካሄዳቸው ነው የተገለጸው፡፡

ሀገሪቷ የምኅንድስና ትምህርትን ለማስፋፋት በፈረንጆቹ 2016 ዕቅድ እንደነበራትና በቀጣዩ ዓመት ይፋ እንዳደረገች፣ እንዲሁም በፈረንጆቹ 2018 ላይ የሀገሪቷ ትምህርት ሚኒስቴር የምኅንድስና፣ የግብርና፣ የሕክምና እና የሥነ-ጥበብ ዘርፎችን ለማሳደግ ዕቅድ ተነድፎ ሲተገበር መቆየቱ ተመላክቷል፡፡

በዕቅዱ መሠረት ከሀገሪቷ ታዋቂ ዩኒቨርሲቲዎች አንዱ የሆነው ፔኪንግ ዩኒቨርሲቲ ቀዳሚ በመሆን እርምጃዎችን መውሰዱን ነው ሹ ሻይፒንግ የተናገሩት፡፡

በፈረንጆቹ 2019፣ ዩኒቨርሲቲው የሰው ሰራሽ አስተውህሎት ኢኒስቲትዩት ማቋቋሙም የተመላከተ ሲሆን ÷ ዩኒቨርሲቲው የቁስ አካላዊ ሣይንስ እና ምኅንድስና እንዲሁም የቴክኖሎጂ ትምህርቶችንም በፈረንጆቹ 2020 መጀመሩን ጠቅሰዋል – ሊቀ-መንበሩ፡፡

ምንጭ ÷ ሲጂቲ ኤን

በዓለማየሁ ገረመው

 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.