Fana: At a Speed of Life!

የምንኖረውም ሆነ መስዋዕትነት የምንከፍለው ለሀገርና ለህዝብ ነው- የሰራዊት አባላት

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ወታደር የሚኖረውም ሆነ መስዋዕትነት የሚከፍለው ለሃገር እና ለህዝብ ነው ሲሉ የብርሸለቆ መሰረታዊ ውትድርና ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት የሰራዊት አባላት ተናገሩ።
ሰራዊቱ ከቤተሰቡና ኑሮው ቅድሚያ ለሀገሬና ህዝቤ በማለት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል የተሰጠውን ህገ-መንግስታዊ ተልዕኮ በላቀ ውጤት እየፈጸመ ነው ሲሉ ሻለቃ ገመቹ አሰፋ ተናግረዋል፡፡
ሰራዊቱ በዱር በገደሉ ደሙን አፍስሶ አጥንቱን ከስክሶ ህይወቱን ለሃገሩ በመክፈል÷ ሃገር ተረጋግታ እንድትቀጥል እያደረገ ነውም ብለዋል፡፡
ሻምበል መሃመድ ሲራጅ በበኩላቸው÷ በአሁኑ ወቅት ሰራዊቱ የተቃጣበትን ሀገር የማፍረስ ሴራ በመቀልበስ የሽብርተኛ ቡድኑን አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት የህዝብ አለኝታ መሆኑን በግልፅ አረጋግጧል ብለዋ፡፡
ህዝባችንም ከሰራዊቱ ጎን በመቆም ደጀንነቱን እየረጋገጠ ነው ብለዋል፡፡
መቶ አለቃ እናየ በለጠ እና አስር አለቃ ዳንኤል ሰለሞንሌሎች የሠራዊቱ አባላት ደግሞ÷ ውትድርና ከየትኛውም የተለየ የተከበረ ሙያ ነው፤ በውትድርና ሙያ ውስጥ ውድ ህይወትን መስጠት እንጂ መቀበል የለም ብለዋል፡፡
ሀብታችን ሃገራችንና ህዝባችን ነው÷ በውትድርና ህይወት ለራሴ ብለህ የምትቀንሰው ቀን የለም፤ ዛሬም የእናት ጡት ነካሾችን ለመደምሰስ ግዳጃችንን በመወጣት ላይ እንገኛለን ማለታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት የማህበራዊ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.