Fana: At a Speed of Life!

የምክር ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች የተቃጣውን አገር የማፍረስ አደጋ ለመመከት ዝግጁ መሆናቸውን አስታወቁ

 

አዲስ አበባ፣ ህዳር 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ “ኢትዮጵያ” የሚለውን የነጻነት ስም የማስጠበቅ የታሪክ አደራ አለብን በሚል ያስተላለፉትን መልዕክት ተከትሎ ነው ከፍተኛ አመራሩ ዝግጁነቱን ያስታወቀው፡፡

የብልጽግና ፓርቲ ትናንት ባካሄደው ስብሰባ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በጦር ግንባር በመገኘት ጦሩን ለመምራት እንደሚሄዱ አስታውቀው በዛሬው ዕለትም ወደ ግንባር ተጉዘዋል፡፡

ይህን በአገር ላይ የተደቀነውን አገር የማፍረስ አደጋ ለመመከት በጦር ግንባር ሆኖ ህይወቱን እየገበረ ካለው ሠራዊት ባልተናነሰ ኢኮኖሚውን ለማዳከም በተከፈተው ሌላው ጦርነት ከፍተኛ አመራሩ በመረባረብ ሊቀለብሰው እንደሚገባም ነው የተገለፀው፡፡

ከፍተኛ አመራሩ ዛሬ ባደረገው ስብሰባም ይህንኑ መነሻ በማድረግ እንደ አገር የተቀመጠውን አቅጣጫ እውን ለማድረግ የሥራ ስምሪት ወስዷል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ነገ በሚጀመረው የቋሚ ኮሚቴ አመታዊ የእቅድ ግምገማ ይህንኑ አቅጣጫ መሠረት በማድረግ እንደሚካሄድ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.