የምዕራባውያንን ጣልቃ ገብነት የሚቃወም ሰልፍ በዓላማችን ዋና ዋና ከተሞች የፊታችን እሁድ ይካሄዳል
አዲስ አበባ፣ ህዳር 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ምዕራባውያን አገራት በኢትዮጵያ ላይ የሚያደርጉትን ጣልቃ ገብነት እና ጫና የሚቃወም ዓለም አቀፍ ሰላማዊ ሰልፍ የፊታችን እሁድ ሕዳር 12 ቀን 2014 ዓ.ም እንደሚካሄድ ተጠቆመ።
ሰልፉ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ማህበረሰብ ከኢትዮጵያ ሕዝብ እና መንግስት ጎን መቆሙን የሚያረጋግጥበት ነው ተብሏል።
የዓለም አቀፉ የተቃውሞ ሰልፍ አስተባባሪ ኮሚቴ አባል አቶ ከባዱ ሙሉቀን ለኢዜአ እንደተናገሩት፥ ሰልፉ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ምዕራባውያን አገራት በኢትዮጵያ ላይ የሚያደርጉትን ጣልቃ ገብነት እንደሚቃወሙ ድምጻቸውን በአንድነት ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የሚያሰሙበት ነው፡፡
በሰሞኑ በዋሺንግተን ዲሲ፣ቶሮንቶ እና ብራሰልስ ተመሳሳይ ዓላማ ያነገቡ ሰልፎች መካሄዳቸውን አስታውሰው፤ የኢትዮጵያ ድምጽ ጎልቶ እንዲሰማ በማሳብ ዓለም አቀፍ ይዘት ያለው ሰልፍ ለማካሄድ ዝግጅት መደረጉን ተናግረዋል።
እሁድ ሕዳር 12 ቀን 2014 ዓ.ም የሚካሄደው ዓለም አቀፍ የተቃውሞ ሰልፍ በዓላማችን በሚገኙ ዋና ዋና ከተሞች ላይ እንደሚካሄድ ነው የጠቆሙት።
ዋሺንግተን ዲሲ፣ አትላንታ፣ ኒውዮርክ፣ ቶርንቶ፣ ካልጋሪ፣ ጆሀንስበርግ፣ ቴልአቪቭ፣ ቶኪዮ፣ ሲድኒ፣ ለንደን፣ ኮሎራዶና ቺካጎ እሁድ ሰልፎቹ ከሚካሄድባቸው ከተሞች መካከል ይገኙበታል።
በዕለቱ ሰልፍ የሚካሄድባቸው ሌሎች ከተሞች በቀጣይ ቀናት ይፋ እንደሚሆኑ ነው አቶ ከባዱ የገለጹት።
የጊዜ አቆጣጠርን ታሳቢ ባደረገ መልኩ ሰላማዊ ሰልፉ በየከተሞቹ በተመሳሳይ በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከቀኑ 7 ሰዓት ጀምሮ መካሄድ እንደሚጀምርም ጠቁመዋል።
የዓለም አቀፉ ሰልፍ አካል የሆነው ተቃውሞ በሞንትሪያል እና በኦቶዋ ከተሞች ቅዳሜ ሕዳር 11 ቀን 2014 ዓ.ም እንዲሁም በናሽቪል ከተማ ሕዳር 13 ቀን 2014 ዓ.ም ከተማ እንደሚካሄድም አመልክተዋል።
ሕዳር 16 ቀን 2014 ዓ.ም በጄኔቫ ተመሳሳይ የተቃውሞ ሰልፍ ይካሄዳል ነው ያሉት።
ዓለም አቀፍ ሰልፉ ምዕራባውያን አገራት በኢትዮጵያ ላይ እያደረጉት ያለውን ጫና እና ጣልቃ ገብነት እንዲሁም ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን በኢትዮጵያ ላይ የሚያስተለልፏቸውን የሐሰት ዘገባዎች እንዲያቆሙ የሚያሳስቡ መልዕክቶች እንደሚተላለፉ መግለጻቸውን የኢዜአ ዘገባ ያመለክታል።
በሰልፉ ላይ በውጪ አገር የሚኖሩ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ማህበረሰብ አባላት ከኢትዮጵያ ሕዝብ እና መንግስት ጋር አንድ መሆኑን እንደሚያሳዩም ነው አቶ ከባዱ ያስረዱት።
በሰልፉ ላይ በርካታ ቁጥር ያላቸው ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ-ኢትዮጵያውያን እንዲሁም የኢትዮጵያ ወዳጆች እንደሚሳተፉና በተለያዩ ተወካዮች አማካኝነት ንግግሮች እንደሚደረጉ ጠቁመዋል።
ምዕራባውያን አገራት የኢትዮጵያን እውነት እንዲሰሙና ጣልቃ ገብነታቸውን እንዲያቆሙ ዳያስፖራው ግፊት ማድረጉን ይቀጥላል ነው ያሉት፡፡
ሕዳር 12 ቀን 2014 ዓ.ም የሚካሄደውን ሰላማዊ ሰልፍ ሰላምና አንድነት ማህበር የዋሺንግተን ዲሲ ግብረ ሃይል፣የ#NoMore የትዊተር ዘመቻ እንቅስቃሴ አስተባባሪዎች፣የተለያዩ ተቋማትና አገር ወዳድ ወዳጆች በጋራ እንዳዘጋጁት ተገልጿል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
0
People reached
0
Engagements
–
Distribution score
Boost post
Like
Comment
Share