Fana: At a Speed of Life!

የምዕራባውያን አገራት በአፍሪካ ላይ የሚያደርጉትን ጫና የሚቃወም ሰልፍ በፕሪቶሪያ ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 20 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የምዕራባውያን አገራት በአፍሪካ ላይ የሚያደርጉትን ጫና የሚቃወም ሰልፍ በደቡብ አፍሪካ በፕሪቶሪያ ከተማ ተካሄደ።

ሰልፈኞቹ በፕሪቶሪያ ከተማ በሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ተቃውሟቸውን ያሰሙ ሲሆን፤ ለኤምባሲውም ደብዳቤ አስገብተዋል።

በተመሳሳይም ፕሪቶሪያ በሚገኘው የአውሮፓ ሕብረት መስሪያ ቤት ተቃውሟቸውን እንደሚያሰሙና ደብዳቤ እንደሚያስገቡ ተገልጿል።

በሰልፉ ላይ በደቡብ አፍሪካ ዘጠኝ ግዛቶች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ-ኢትዮጵያውያን፣ ደቡብ አፍሪካውያንን ጨምሮ በአገሪቷ የሚኖሩ የተለያዩ አፍሪካ አገራት ዜጎችና የፓን አፍሪካኒዝም አቀንቃኞች እየተሳተፉ መሆኑ ታውቋል፡፡

በሰልፉ ላይ ምዕራባውያን አገራት ኢትዮጵያን ጨምሮ በአፍሪካ ላይ ለመጫን የሚፈልጉትን ዘመናዊ የቅኝ ግዛት አስተሳሰብ የሚቃወሙ መልዕክቶች አስተላልፈዋል።

ሰላማዊ ሰልፉ አፍሪካውያን ከኢትዮጵያ ጎን እንደሚቆሙ የሚያሳዩበት እንደሆነ ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ሰላማዊ ሰልፉን ያዘጋጁት የተባበሩት የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ማህበር በደቡብ አፍሪካ እና የአፍሪካ ዳያስፖራ ፎረም ናቸው።

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.