Fana: At a Speed of Life!

የምዕራብና ደቡባዊ የአገሪቱ ክፍሎች በሚቀጥሉት 10 ቀናት ዝናብ ያገኛሉ – ሚቲዎሮሎጂ ኤጀንሲ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 3፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) በምዕራብና ደቡባዊ የአገሪቱ ክፍሎች በሚቀጥሉት አስር ቀናት የተለያየ መጠን ያለው ዝናብ የሚያገኙ መሆኑን የብሔራዊ ሚቲዎሮሎጂ ኤጀንሲ አስታወቀ።
ኤጀንሲውን ጠቅሶ ኢዜአ እንደዘገበው፥ በሚቀጥሉት 10 ቀናት በምዕራብና ደቡባዊ የአገሪቱ ክፍሎች የተለያየ መጠን ያለው ዝናብ የሚጠበቅ ይጠበቃል፡፡
በጥቂት የደቡባዊ የአገሪቱ አጋማሽ የተወሰኑ ቦታዎች ላይ ደግሞ ከባድ ዝናብ ሊኖር ይችላል ተብሏል፡፡
የአገሪቱ ክፍሎች በአመዛኙ ደረቅ፣ ፀሐያማና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ይኖራቸዋል ብሏል ኤጀንሲው።
ከኦሮሚያ ጅማ፣ ኢሉአባቦር፣ ሁሉም የወለጋ ዞኖች፣ አርሲና ባሌ ዞኖች፣ የቤንሻንጉል ጉሙዝ ፣ ምዕራብ ትግራይ በአብዛኛው ከመደበኛ ጋር የተቀራረበ ዝናብ እንደሚያገኙ ይጠበቃል።
ከአማራ ክልል የሰሜንና የደቡብ ጎንደር ዞኖች፣ ምዕራብ ጎጃም፣ የባህርዳር ዙሪያ እና አገው አዊ ተመሳሳይ የዝናብ መጠን ይኖራቸዋል ተብሎ ይገመታል።
ከደቡብ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ወላይታ፣ የከፋና ቤንቺ ማጂ፣ የጌዲዮ፣ የጉራጌ፣ የጋሞና ጎፋ ዞኖች እና ከሱማሌ ክልል ፋፈን፣ ቆራይ፣ ዶሎ እና የሸበል ዞኖች በአብዛኛው ከመደበኛ ጋር የተቀራረበ ዝናብ እንደሚያገኙም ተጠቁሟል።
በመጀመሪያዎቹ ጥቂት ቀናት ከሚፈጠረው ደመና በሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ በሰሜን ምዕራብ፣ በምስራቅ አና ደቡብ ትግራይ፣ ከአፋር ክልል ዞን 3 ፣ 4 እና 5 በጥቂት የሰሜን ቦረናና ጉጂ ዞኖች፣ ምስራቅ ሐረርጌ፣ በሐረር፣ በጋምቤላ፣ ደቡብ ኦሞና ሰገን ህዝቦች እንዲሁም በአዲስ አበባ በጥቂት ቦታዎች ላይ አነስተኛ ዝናብ ይኖራል።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.