Fana: At a Speed of Life!

የምዕራብ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ የሰራዊት አባላት የማዕረግ ዕድገት ሰጠ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የምዕራብ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ የመቆያ ጊዜያቸውን ለሸፈኑና በስራ አፈፃፀማቸው ውጤታማ ለነበሩ የሰራዊት አባላት የማዕረግ ዕድገት ሰጠ።
የተሰጠው የማዕረግ ዕድገት ከፍተኛና መስመራዊ መኮንኖችን እንዲሁም ባለ ሌላ ማዕረግተኞችን ያካተተ መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡
የምዕራብ ዕዝ መሃንዲስ መምሪያ ሀላፊ ኮ/ል ግርማ ወንዳፍራሽ እንደገለጹት÷ የማዕረግ ዕድገት ጊዜ ተቆጥሮ የሚሰጥ ሳይሆን÷ ሀላፊነት በአግባቡ በመወጣት የሚሰጥ በመሆኑ በተወጣችሁት ተልዕኮና በዲሲፒሊናችሁ ተመዝናችሁ የሚሰጥ ነው፡፡
በሃገራችን ላይ የተቃጣውን የውስጥና የውጭ የሰላም ስጋት እስከመጨረሻው ለማጥፋት እየተሰራ ባለው ያልተቋረጠ ስራ ተሿሚዎች ሚናቸውን በአግባቡ መወጣት እንዳለባቸውምነው የመምሪያው ኃላፊ ያሳሰቡት፡፡
የምዕራብ ዕዝ የሰው ሃብት አመራር መምሪያ ተወካይ ሃላፊ ሻምበል አየነው አዱኛ በበኩላቸው÷ የማዕረግ እድገት የሚሰጥባቸውን አግባቦችና አስፈላጊነት አብራርተዋል፡፡
የማዕረግ ተሿሚዎችም÷ በቀጣይ የሚሰጣቸውን ሀላፊነትና ግዳጅ በአግባቡ ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን መናገራቸዉን ከመከላክያ ሰራዊት ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.