Fana: At a Speed of Life!

የምገባ መርሃ-ግብር ተግባራዊ መሆን ወደ ትምህርት ገበታ የሚመጡ ተማሪዎችን ቁጥር እንዲጨምር አድርጓል

አዲስ አባባ፣ መስከረም 28፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) የተማሪዎች ምገባ መርሃ-ግብር ተግባራዊ መሆን በዘንድሮው የትምህርት ዘመን ወደ ትምህርት ገበታ የሚመጡ ተማሪዎችን ቁጥር እንዲጨምር ማድረጉን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተማሪዎች ምገባ ኤጀንሲ አስታወቀ።

ኤጀንሲው በዘንድሮው ትምህርት ዘመን ከ1 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር በላይ በጀት በመያዝ በሁሉም የቅድመ መደበኛና የመጀመሪያ ደረጃ የመንግስት ትምህርት ቤቶች ምገባ ለማድረግ ዝግጅቱን ማጠናቀቁንም ገልጿል።

በእያንዳንዱ ምርት ላይ እየተስተዋለ ያለውን የዋጋ ጭማሪ ታሳቢ በማድረግ ተጨማሪ 80 ሚሊየን ብር መመደቡንም እንዲሁ።

የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ኢሳያስ ምህረት እንደተናገሩት፤ የመርሃ ግብሩ ተግባራዊ መሆን ወላጆች በመንግስት ትምህርት ቤቶች ላይ መተማመን እንዲኖራቸው ከማድረጉም ባሻገር መጠነ መቋረጥ እንዲቀንስ አድርጓል ነው ያሉት።

በዚህም በ2013 የመርሃ ግብሩ አተገባበር ላይ የታዩ ክፍተቶችን በመለየት ከ240 በላይ ተጨማሪ የመመገቢያና የማብሰያ አዳራሽ ተገንብተዋል ብለዋል።

በመርሃ ግብሩ ለሚሳተፉ 10 ሺህ እናቶች የኮቪድ-19 ክትባት እንደተሰጣቸውም ተናግረዋል።

የምገባ መርሃ-ግብሩ በዘንድሮው የትምህርት ዘመን ከ40 ሺህ በላይ ተጨማሪ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታ እንዲመጡ ማድረጉንም ነው ዋና ዳይሬክተሩ የተናገሩት።

የምገባ መርሃ-ግብሩ ጥቅም 1 ቀን 2014 ዓ.ም እንደሚጀምር መጠቆማቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የተማሪዎች የደንምብ ልብስ ትምህርት በተጀመረ በሳምንት ጊዜ ውስጥ ተሰራጭቶ እንደሚጠናቀቅ ጠቅሰው፤ እስካሁን ባለው ጊዜ ከ1 ነጥብ 4 ሚሊዮን በላይ ደብተር ለተማሪዎች መሰጠቱን ተናግረዋል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.