Fana: At a Speed of Life!

የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ የምንችለው የግብርና ምርትና ምርታማነትን ስናሳድግ ነው- አቶ ሙስጠፌ መሀመድ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) “የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ የምንችለው የግብርና ምርትና ምርታማነት ስናሳድግ እና የእርሻ መሬትን ስናለማ ብቻ ነው” ሲሉ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሀመድ ገለጹ፡፡
በሶማሌ ክልላዊ መንግስት የገዛቸውን 100 የግብርና ሜካናይዜሽን ትራክተሮችን ዛሬ የተረከበ ሲሆን÷ ትራክተሮቹ በክልሉ እየተከናወነ ያለውን የግብርና ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ ከፍተኛ አስታውጽኦ እንዳላቸው ተገልጿል፡፡
በመርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሀመድ÷ የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ የምንችለው የግብርና ምርትና ምርታማነት ስናሳደግና የእርሻ መሬትን ስናለማ ብቻ ነው ብለዋል።
ወደ ክልሉ የገቡ የግብርና ሜካናይዜሽን መሳሪያዎችን እና በቀጣይም ክልሉ የሚረከባቸውን የግብርና መሳሪያዎችን በአግባቡ መጠቀም አንደሚያስፈልግም አሳስበዋል፡፡
የክልሉ አርሶ አደሮችና ከፊል አርብቶ አደርች የዚህ ዘመናዊ የግብርና ስርዓት ተጠቃሚ ከሆኑ፥ የሶማሌ ክልል ሕዝብ ምርታማነት በእጥፍ እንደሚጨምር ንው አቶ ሙስጠፌ ያስረዱት።
የክልሉ መንግስት በግብርና ምርት ላይ ትኩረት መስጠቱን ጠቅሰው÷ የክልሉ ማህበረሰብ የመሬት ሃብቱን በተለይም የሰብል ምርትና ምርታማነትን በአግባቡ እንዲጠቀምና ከእርዳታ ጠባቂነት እንዲላቀቅም አሳስበዋል።
የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር አብዲቃድር ኢማን በበኩላቸው÷ ትራክተሮቹ በክልሉ የግብርና ምርት ላይ ትልቅ ሚና እንደሚጫወቱ ገልፀው÷ የተገኙት የግብርና ሜካናይዜሽን መሳሪያዎች የአርሶ አደሩ ምርት እና ምርታማነት እንዲጨምር ያግዛሉ ብለዋል፡፡
በመሬት ሀብታቸው ላይ ትኩረት ለሚያደርጉ የክልሉ አርሶ አደሮች ትራክተሮች በብድር መልክ እንደሚሰጡ ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.