Fana: At a Speed of Life!

የረመዳን ጾምን በመተሳሰብ እና በመተዛዘን ማሳለፍ ይገባል – ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጅ ዑመር እድሪስ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 30 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የረመዳን ጾምን በፍቅር፣ በመተሳሰብ እና በመተዛዘን ማሳለፍ እንደሚገባ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር እድሪስተናገሩ፡፡

ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጅ ዑመር እድሪስ በሰጡት መግለጫ ወሩን በመተሳሰብ፣ በመተጋገዝና በመተዛዘን ማሳለፍ ይገባል ብለዋል፡፡

ከወንጀል እና ከበደል በመቆጠብም ወደ አምላክ መቅረብ እንደሚያስፈልግም አንስተዋል፡፡

በመግለጫው በተለያዩ አካባቢዎች የሚስተዋለውን የዜጎችን ሞትና መፈናቀል አውግዘው፥ መንግስትና ህግ አስከባሪ አካላት የዜጎችን ደህንነት ከማስጠበቅ አንጻር ሃላፊነታቸውን እንዲወጡም ጠይቀዋል፡፡

የሃይማኖት አባቶች ህዝቡን ማስተማር ይገባቸዋል ያሉት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጅ ዑመር እድሪስ፥ ለአንድነትና ለሰላም ሁሉም ሃላፊነቱን እንዲወጣም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በማህሌት ተክለብርሃን

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.