Fana: At a Speed of Life!

ሰርጌ ላቭሮቭ ለአቶ ደመቀ መኮንን የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሩሲያዉ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ለምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የዉጭጉዳይ ሚንስትር አቶ ደመቀ መኮንን የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
አቶ ደመቀ መኮንን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው በመቀጠልዎ የተሰማኝ ደስታ ለመግለጽ እወዳለሁ ብለዋል ሰርጌ ላቭሮቭ፡፡
የሩሲያ እና የኢትዮጵያን ግንኙነት ለማስፋት በፖለቲካ፣ በንግድ በኢኮኖሚ እና በሌሎች ዘርፎች ትብብርን ለማጎልበት እና የሃገራቱን ህዝቦች ጥቅም ለማስጠበቅ ዝግጁ መሆናቸዉን ገልጸዋል፡፡
በአፍሪካ ቀንድ እና በአጠቃላይ በአፍሪካ አህጉር ውስጥ መረጋጋትን እና ደህንነትን ለማጠንከርም አብረን እንሰራለን ብለዋል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.