Fana: At a Speed of Life!

ሩሲያ የመጀመሪያው የኮሮና ቫይረስ ክትባት ጥቅም ላይ እንዲውል ወሰነች

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 5 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ ) የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሜር ፑቲን በዓለም ላይ የመጀመሪያው የኮሮና ቫይረስ ክትባት ጥቅም ላይ እንዲውል መወሰኑን አስታወቁ።
 
ክትባቱ በሞስኮ ጋመሌያ ኢንስቲቱዩት የተዘጋጀ መሆኑ የተነገረ ሲሆን በዛሬው ዕለትም ከሀገሪቱ ጤና ሚኒስቴር ማረጋገጫን አግኝቷል።
 
ፕሬዚዳንቱም ሩሲያ በቅርብ ጊዜያት የኮሮና ቫይረስ ክትባቱን በብዛት ማምረት እንደምትጀምር ገልፀዋል።
 
ፑቲን የመጀመሪያውን የኮሮና ቫይረስ ክትባት ልጃቸው መውሰዷን መናገራቸውን የኢንደፔንዳትና አርቲ ዘገባ ያመለክታል።
 
ልጃቸው ክትባቱን ከወሰደች በኋላ መጠነኛ ሙቀን እንደነበራት የገለፁቱት ፕሬዚዳንቱ ከቆይታ በኋላ ግን መጠነኛ ሙቀቱ መጥፋቱን ተናግረዋል።
 
#FBC
 
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.