Fana: At a Speed of Life!

የሰላም ሚኒስቴር በአፋር ክልል ከተለያዩ የማህበረሰብ አካላት ጋር ተወያየ

አዲስ አበባ ፣ታህሳስ 26 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሰላም ሚኒስቴር የህግ ማስከበር ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ወይዘሮ ፍሬአለም ሽባባው የተመራው ልዑክ በአፋር ክልል ከተለያዩ የየማህበረሰብ አካላት ጋር ውይይት አካሄደ፡፡
የልዑካን ቡድኑ ከጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት፣ ከፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን እንዲሁም ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ የተውጣጡ የአመራርና የባለሙያዎች ቡድንን ያካተተ መሆኑ ተገልጿል።
ቡድኑ የአፋርና የኢሳ ብሔረሰብ ተወካዮችን በማግኘት በገዋኔ፣ በአሩካ እና በእንደፎ ከተሞች ውይይት አድርጓል፡፡
በወቅቱም ሚኒስትር ዲኤታዋ መንግስት የተከሰተውን ችግር ለመፍታት በትኩረት እየሰራ መሆኑን ገልጸው÷ ለተፈናቀሉ፣ ከትምህርት ለተስተጓጎሉና ወላጆቻቸውን ላጡ ህጻናት፣ ሴቶችና አቅመ ደካሞች ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር አስፈላጊውን ድጋፍና እንክብካቤ እንዲያገኙ ያደርጋል ብለዋል፡፡
የውይይቱ ተሳታፊ የማህበረሰብ ተወካዮች ከጸጥታ ኃይል አባላት ጋር በመተባባርና በመተጋገዝ ለሰላም እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል።
በውይይቱ ለተሳተፉ የማህበረሰ ተወካዮች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሀይማኖት አባቶች፣ ወጣቶች፣ ሴቶችና ህጻናት ጥሪውን አክብረው ስለተገኙ ምስጋና ማቅረባቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People Reached
0
Engagements
Boost Post
Like

 

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.