Fana: At a Speed of Life!

የሰላም ሚኒስቴር ከሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ጋር በሚያከናውኗቸው የተግባር እቅድ ላይ ተወያየ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 20 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰላም ሚኒስቴር ከሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ጋር በጋራ በመሆን በሚያከናውኗቸው የተግባር እቅድ ላይ ተወያይተዋል፡፡

የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል ሰላማዊ የሆነ ሲቪል ሰራተኛ በመገንባት ህብረተሰቡን ማገልገል የሚችልና ዜጋውን የመገንባት አቅም ያለው የመንግስት ሰራተኛ ለመፍጠር ይቻል ዘንድ ከተቋሙ ጋር በጋራ መስራት አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱን አንስተዋል፡፡

በልዩ ድጋፍና አርብቶ አደር አካባቢዎች የሰው ሀይል ማሟላትና ክትትል ማድረግ፣ የብሔራዊ በጎ ፍቃድ ማህበረሰብ አገልግሎት ተሳታፊዎች ድጋፍና ክትትል ማድረግ፣ ለህዝብ አገልግሎት በሚሰጡ ተቋማት የሰላም ግንባታ ስራዎችን ማከናወን የሚሉ ጉዳዮች በሁለቱ ተቋማት የጋራ እቅድ ላይ ተካቷል፡፡

የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ በዛብህ ገብረየስ የጋራ እቅዱ በጋራ ለሚከናወኑ ተግባራት ሀላፊነትን መወጣት የሚያስችል እንደሆነ መናገራቸውን የሰላም ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.