Fana: At a Speed of Life!

የሰላም ሚኒስቴር ያዘጋጀው ህብረተሰብ ዓቀፍ የውይይት እና የተሳትፎ መድረክ ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 21 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰላም ሚኒስቴር ያዘጋጀው ህብረተሰብ ዓቀፍ የውይይት እና የተሳትፎ መድረክ ተካሄደ ።
 
በዚህ ወቅት የሰላም ሚኒስቴር ዲኤታ አቶ አለማየሁ እጅጉ ኢትዮጵያ የጀመረችውን የለውጥ ግስጋሴ መንከባከብና ወደ ላቀ ደረጃ ማሸጋገር የሁሉም ታሪካዊ ሃላፊነት መሆኑን ተናግረዋል።
 
የምክክር መድረኩ በሰፊ ሃገራዊ ምክክር ሂደት ውስጥ የአመራሩን ሚና ዴሞክራሲያዊና አጋዥ ማድረግ፣ የለውጡ እሳቤ መዋቅራዊ ገጽታና አፈጻጸም ሂደት መሰረቶች ላይ ግንዛቤ ማዳበር እንዲሁም ከምክክር መድረኩ የተቀሰመውን ይዘትና ዘዴ ለአጋሮች ለማስተላለፍ እድል ማመቻቸትን ዓላማው አድርጓል፡፡
 
የምክክር መድረኩ ለሶስት ቀናት የሚቆይ ሲሆን አስተሳሰብና የስሜት ብልህነት ላይ ስልጠና፣ የሰላም ፖሊሲ፣ የብሄራዊ ምክክር ቅርጽ እና ሂደት ዙሪያ ጥናታዊ ጽሁፍና ውይይት ተደርጓል፡፡
 
ከዚህ ባለፈም የህግ የበላይነት እና የዜጎች ክብር እንዲሁም ተዛማጅ ርዕሶች ላይ ውይይት እንደሚካሄድ የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡
 
በምክክር መድረኩ ላይ የክልል፣ የከተማ አስተዳደር፣ የዞን እና የወረዳ አመራሮች ተሳትፈዋል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.