Fana: At a Speed of Life!

የሰላም ጥሪውን ያልተቀበሉ የተላላኪው ሸኔ አባላትን የመደምሰሱ ሂደት ተጠናክሮ ቀጥሏል- አቶ አዲሱ አረጋ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰላም ጥሪውን ያልተቀበሉ የተላላኪው ሸኔ አባላትን የመደምሰሱ ሂደት ተጠናክሮ መቀጠሉን በኦሮሚያ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የከተሞች ክላስተር አስተባባሪ አቶ አዲሱ አረጋ ተናግረዋል።
 
በሰሜን ሸዋ ዞን ፍቼ ከተማ የሰላምና የልማት ኮንፈረንስ በዛሬው ዕለት ተካሂዷል፡፡
 
በኮንፈረንሱ አቶ አዲሱ አረጋን ጨምሮ የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ታዬ ደንደኣ፣ የፌደራልና የክልል የስራ ሃላፊዎች አባገዳዎች፣ ሃደ ሲንቄዎች እና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል፡፡
 
ለውይይት መነሻ ጽሁፍ ያቀረቡት የመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ብርሃኑ ሌንጂሶ÷ በሀገር ግንባታ ታሪክ የሰላሌ ህዝብ ሀገርን ከህልውና አደጋ በመታደግ ሂደት ውስጥ ወሳኝ ሚና ሲጫወት መቆየቱን አውስተዋል።
 
በኮንፈረንሱ አሸባሪው ሸኔ እያደረሰ ያለው ጥቃት ለህዝብ ያልወገነ እና የኦሮሞን ህዝብ ለማዋረድ ብሎም ኢትዮጵያን ለማፍረስ የተነሳ ስለመሆኑ የጋራ መግባባት ላይ የተደረሰ ሲሆን ÷ ቡድኑን ለማጥፋትም ውስጥን ማፅዳት ተገቢ መሆኑ ተገልጿል።
 
በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ቡድኑን የተቀላቀሉ ዜጎች ከህብረሰተሰቡ የወጡ እንደመሆናቸው የሰላም አማራጭን እንዲከተሉ ጠንካራ ስራ እንዲሰራም ተጠይቋል።
 
በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የከተሞች ክላስተር አስተባባሪ አቶ አዲሱ አረጋ በበኩላቸው÷ መንግስት የሸኔ አሸባሪ ቡድንን ለማጥፋት ቁርጠኛ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
 
ለዚህም ህብረተሰቡ የቡድኑን አባላት ከማጋለጥ ጀምሮ በርካታ ስራዎችን መስራት እንደሚጠበቅበት ነው ያስገነዘቡት፡፡
 
ሰላምን ምርጫው ያላደረገ የሽብር ቡድኑን አባል ግን ለመደምሰስ መዘጋጀት የመጨረሻው አማራጭ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
 
የኮንፈረንሱ ተሳታፊዎችም የሽብር ቡድኑን ለመደምሰስ እና የሀገርን ህልውና ለመታደግ በሙሉ አቅም ለመስራት መነሳታቸውን በማጠቃለያ ባወጡት የአቋም መግለጫ አሳውቀዋል።
 
ተሳታፊዎቹ ዜጎችን እየገደለ፣ ንብረት እያወደመ፣ የሽብር ቡድኑን ህወሓት ተልዕኮ እየፈፀመ ያለውን ሸኔን መደምሰስ ግድ የሚልበት ወቅት ላይ ነን፤ ለዚህም ዝግጁ ነን ብለዋል።
 
በሀብታሙ ተክለስላሴ
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.