Fana: At a Speed of Life!

የሰሜን ወሎዋ ጋሸና ከተማ ተቋርጦባት የቆየውን የኤሌክትሪክ ኃይል አገኘች

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 18 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ወራሪው ህወሓት ለአምስት ወራት በቆየባቸው ጊዜያት ከፍተኛ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ውድመት ያደረሰባት ጋሸና ከተማ ተቋርጦባት የነበረውን የኤሌክትሪክ ኃይል በዛሬው እለት አገኘች።
አካባቢው ጠላት ለረዥም ጊዜ የቆየበት ሲሆን ከደብረ ዘቢጥ እስከ ጋሸና ያለው የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት በከፍተኛ ሁኔታ የተጎዳ ቢሆንም በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የስራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች ርብርብ የመካከለኛና ዝቅተኛ መስመር ጥገና ተጠናቆ ኃይል መስጠት ተችሏል።
በአካባቢው ያሉ ሌሎች ከተሞች የመካከለኛና ዝቅተኛ መስመር ጥገና እየተሰራ ሲሆን፥ በነገው እለት ፍላቂት፣ ገረገራ፣ ኮን እና በአካባቢው ያሉ ከተሞች የተቋረጠባቸውን ኃይል መልሰው እንደሚያገኙ የወልዲያ ዲስትሪክት ዳይሬክተር ገልፀዋል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.