Fana: At a Speed of Life!

የሰሞኑ ጉንፋን ጉዳይ!

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)  ሰሞኑን ወረርሽ በሚመስል መልኩ በርካቶች በዚህ ህመም ተይዘዋል። የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታልም ለዚህ የሰሞኑ ጉንፋን ጠቃሚ መረጃን በማህበራዊ ትስስር ገፁ ይዞ ወጥቷል።

የሰሞኑ ጉንፋን ለየት የሚያረገው ግን ከፍተኛ ትኩሳት እና ጠንከር ያለ ሳል አለው በተጨማሪም እነዝህ ምልክቶች ይታዩበታል፡፡

  • ብርድ ብርድ ማለት
  • የመገጣጠሚያ ህመም
  • የጀርባ ህመም
  • የጡንቻ ህመም
  • ምግብ ፍላጎት መቀነስ
  • ኃይለኛ ራስ ምታት
  • ፍዝዝ ማለት

ምክንያቱ ምን ሊሆን ይችላል?

ጉንፋን ዋና መንስኤዎቹ በትንፋሽ በሳል እና በማስነጠስ የሚተላለፉ ቫይረሶች ናቸው ::ለምሳሌ÷ ኮሮና ቫይረስ ፣ራይኖ ቫይረስ፣ ኢንፍሉዌንዛ አዴኖ ቫይረስ እና የመሳሰሉት ጉንፋንን ሊያመጡ ይችላሉ፡፡ስለዚህ የሰሞኑ ጉንፋን ኮሮና ይሁን አይሁን የሚታወቀው በምርመራ ብቻ ነው:: ስለዚህ ምን እናድርግ?

  • የመከላከያ መንገዶቹን ይተግብሩ
  • ሁሌም የአፍ እና አፍንጫዎን ይሽፍኑ
  • የእጅ እና አካል ንክኪ ይቀንሱ
  • ሰዉ የሚሰበብበት ቦታ አይገኙ
  • ስያስሉ እና ሲያስነጥሱ አፍ እና አፍንጫዎን በክንድዎ/በጨርቅ ይሸፍኑ
  • መንግስት በነፃ ያቀረበውን የኮሮና ክትባትን ይውሰዱ

ለልጆች እና ህፃናት የቤት ዉስጥ ሕክምናው ምንድነው?

  • ለብ ያለ ዉሃ ዉስጥ ትንሽ ጨው አርጎ አፍንጫቸው ቀዳዳ ዉስጥ 2 ጠብታ ማድረግ በመቀጠልየአፍንጫ ቀዳዳዎችን በመምጠጫ ማጽዳት
  • ትኩሳትን የሚቀንስ መድሃኒት መጠቀም ፣
  • ትኩስ ትኩስ ነገሮችን ማጠጣት
  • ተጨማሪ ምግቦችን በደንብ መመገብ
  • የሕፃኑን ክፍል በደንብ ማፅዳት ማናፈስ
  • ቤቱን በውሀ እንፋሎት ማጠን
  • ንፍጥ እና ትኩሳት በጣም አስፈላጊ ፈሳሾችን እና ንጥረ ነገሮችን ይዘው ስለሚወጡ ተጨማሪ ፈሳሽ ነገሮችን ማግኘት ይኖርባቸዋል ::

ለታዳጊ ህፃናት እና ለአዋቂዎችስ የቤት ዉስጥ ሕክምናው ምንድነው?

ከላይ ከተዘረዘሩት በተጨማሪ ራስን በአንድ ክፍል ማግለል

ትኩስ ፈሳሽ ነገሮችን ደጋግሞ መውሰድ

ነጭ ሽንኩርት ማር እና ዝንጅብል መጠቀም

በቂ እረፍት ማድረግ

የትኩሳት እና ራስ ምታት ማስታገሻ መውሰድ

እነዚህን መፍትሄዎ እያረጋችሁ ምንም ለውጥ ከሌለው እና ሳሉ የመባስ ትኩሳቱ የመጨመር ባህሪ ካለው ወይም ትንፋሽ የማጠር ምልክት በህፃንም ሆነ በአዋቂ ላይ ካለ በአፋጣኝ ሆስፒታል መሄድ ያስፈልጋል፡፡

 

በዶ/ር ፋሲል መንበረ  በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ ረዳት ፕሮፌሰር እና የሕጻናት ስፔሻሊስት ሐኪም

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.