Fana: At a Speed of Life!

የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከ15 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ ለአጣዬ ተፈናቃዮች አስረከበ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 3 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስተባብሮ ያሰባሰበውን ከ15 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶች ድጋፍ ለአጣዬ ተፈናቃዮች አስረክቧል።

ድጋፉን ለአጣዬ ከተማ ያስረከቡት በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የአሰሪና ሠራተኛ ጉዳይ ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ወይዘሮ አየለች እሸቴ የገጠመው ችግር የሚታለፍ በመሆኑ ተጋግዘን እንሻገረዋለን ብለዋል ።

ተጎጂዎችም ከደረሰባቸው የስነ ልቦና ጫና በማገገም ከአካባቢው አስተዳደር ጋር ተባብረው ሰላማቸውን እንዲያስጠብቁ ጠይቀዋል ።

ተጎጅዎች በበኩላቸው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ላደረገላቸው ድጋፍ አመስግነው አጠቃላይ ለተጎጅዎች እየተደረገ ያለው ድጋፍ ግን በፍትሃዊነት እየተሰራጨ ባለመሆኑ እንዲስተካከል ጠይቀዋል።

የሰሜን ሸዋ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ብርሃኑ ታዬ በበኩላቸው ተጎጅዎችን መልሶ ለማቋቋም ዐብይና ቴክኒክ ኮሚቴ ተዋቅሮ እየሰራ መሆኑን ገልፀው፥ አሁን ላይ ቤቶችን ለመገንባት የአማራ ክልል ደን ኢንተርፕራይዝ በሰጠው ከ52 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ የደን ዛፍ እየተቆረጠ ነው ብለዋል ።

ከድጋፍ ስርጭቱ ጋር በተያያዘ ያለው የአቅርቦት ችግር ሳይሆን ተጎጅዎችን በትክክል ከመለየት እና ከተጎጂው በኩል አላግባብ ልጠቀም ባይነት የተፈጠረ መሆኑን በመግለፅ ችግሩን ለመፍታት በዞኑ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ተጠሪ ፅህፈት ቤት ሀላፊ የሚመራ ኮሚቴ እየሰራ መሆኑንም አስረድትዋል።

በአበበ የሸዋልዑል

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.