Fana: At a Speed of Life!

የሰርግ ፕሮግራም ሰርዤ ወደ ግንባር ለመዝመት ወስኛለሁ – ረ/ፕሮፌሰር አክሊሉ አይዛ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያን ለማፍረስ ለተዘጋጀው የአሸባሪ ህወሓት ቡድን ምላሽ ለመስጠት በጥር ወር የያዙትን የሰርግ ፕሮግራም ሰርዘው ወደ ግንባር ለመዝመት መወሰናቸውን በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ መምህር የሆኑት ረዳት ፕሮፌሰር አክሊሉ አይዛ ገለጹ።

በአሁን ሰዓት ኢትዮጵያ ከውስጥም ሆነ ከውጭ ወራሪ ኃይል ጥቃት እየደረሰባት ከመሆኑም ባሻገር ሀገር ለማፍርስ ለተዘጋጁት የአሸባሪው የህወሓት ቡድን ጥቃት ከዜጎቿ ምላሽ እንደሚያስፈልጋት ረዳት ፕሮፌሰሩ ገልጸዋል፡፡

ከዚህ ቀደም በዘመቻው ላይ ለመሳተፍ ያቀዱ ቢሆንም÷ የ2ኛ ዲግሪ ተማሪዎችን ሲያግዙ የቆዩና አሁን ተማሪዎቹ እንደተመረቁ የዘመቻ ደብዳቤ ለዩኒቨርስቲው አቀርበው ዝግጅት ላይ መሆናቸውንም መምህሩ ተናግረዋል፡፡

በዲሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠው መንግስት ሀገርን እንዳይመራ እያደረገ ያለውን ጠላት ለመመከት በጥር ወር የያዙትን የሰርግ ፕሮግራም ሰርዘው ወደ ግንባር ለመዝመት መወሰናቸውን አብራርተዋል፡፡

እናቱን የሚጠላ ኢትዮጵያዊ እንደማይኖር የገለፁት መምህሩ÷ አሸባሪው የህወሓት ቡድን በሴራ የሚያምን በመሆኑ ከመንግስት ጎን በመቆም ጦርነቱን በድል ተወጥተን ወደ አንድ ምዕራፍ የምንሸጋገርበት ወቅት ላይ እንገኛለን ብለዋል፡፡

የውጭ ሚዲያዎች የሚያደርጉት ዘመቻ ከዚህ ቀደም ከአሸባሪው ህወሓት የሚያገኙትን ጥቅም የሚያስቀርባቸው በመሆኑ÷ የውሸት ፕሮፓጋንዳቸውን ቢያሰራጩም ይህ በኢትዮጵያዊያን አንድነት እንደሚቀለበስ ረዳት ፕሮፌሰር አክሊሉ ተናግረዋል ሲል ዴሬቴድ ዘግቧል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.