Fana: At a Speed of Life!

የሰብዓዊ እርዳታ የጫኑ በርካታ ተሽከርካሪዎች ወደ ትግራይ እየተጓጓዙ መሆኑን የዓለም ምግብ ፕሮግራም ዳይሬክተር ገለፁ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰብዓዊ እርዳታ የጫኑ በርካታ ተሽከርካሪዎች ወደ ትግራይ ክልል እየተጓጓዙ መሆኑን የዓለም ምግብ ፕሮግራም አስታወቀ፡፡
የዓለም ምግብ ፕሮግራም ዳይሬክተር ዴቪድ ቤስሌይ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ፥በትግራይ ክልል ችግር ውስጥ ለሚገኙ ዜጎች የሚደረገው የሰብዓዊ እርዳታ ተጠናክሮ መቀጠሉን ተናግረዋል፡፡
በዚህ መሰረትም አሁን ላይ ተጨማሪ የሰብዓዊ እርዳታ የጫኑ በርካታ ተሽከርካሪዎች ወደ መቀሌ እያቀኑ እንደሚገኙ ነው ዳይሬክተሩ የገለጹት፡፡
የሚጓጓዘው የሰብዓዊ እርዳታም ባለፉት ወራት በክልሉ በተለያዩ አካባቢዎች በቂ ድጋፍ ያላገኙ በርካታ ዜጎችን ተደራሽ ለማድረግ እንደሚያስችል ጠቁመዋል፡፡
በሒደቱ የመንግስት አመራሮች ትብብር የሚበረታታ መሆኑን የገለጹት ዳይሬክተሩ፥በትግራይ ክልል ችግር ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን ለመታደግ የሚከናወነው ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.