Fana: At a Speed of Life!

የሰኔ ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት ይቀጥላል

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 28፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በግንቦት ወር የነበረው የነዳጅ ምርቶች የመሸጫ ዋጋ የሰኔ ወር የመሸጫ ዋጋ ሆኖ እንዲቀጥል መወሰኑን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ፤ ከግንቦት 28 እስከ ሰኔ 30 ከአውሮፕላን ነዳጅ ውጪ የሌሎች የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት እንደሚቀጥል ነው የተገለጸው።

የአውሮፕላን  የነዳጅ ምርቶች ዋጋ የዓለም የነዳጅ ዋጋን መሰረት በማድረግ ተሰልቶ የተገኘው 11 ሣንቲም በመጨመር በግንቦት ወር ሲሸጥበት ከነበረው 43 ብር ከ81 ሳንቲም ወደ 48 ብር ከ22 ሳንቲም ከፍ እንዲል መወሰኑን ከንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የላከልን መግለጫ  ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.