Fana: At a Speed of Life!

የሰውነትን በሽታ የመከላከል አቅም ለማሳደግ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 9፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰውነትን በሽታ የመከላከል አቅም ማሳደግ በበሽታ እንዳይጠቁ ይረዳወታል።

ባለሙያዎችም የሰውነትን በሽታ የመከላከል አቅም ለማጎልበት ከአመጋገብ ጀምሮ ጤነኛ የህይዎት ዘይቤ መከተል እንደሚገባ ይመክራሉ።

አመጋገብ

በቫይታሚን ሲ የበለጸጉ ምግቦች

በቫይታሚን ሲ የበለጸጉ ምግቦች በተለይም እንደ ጉንፋን ያሉ በሽታዎችን እና መመርቀዝ (ኢንፌክሽንን) ለመዋጋት እና የሰውነትን በሽታ የመከላከል አቅምን ለማጎልበት ይረዳል።

ሎሚ፣ ብርቱካን፣ መንደሪን፣ የወይን ፍሬ እና እንደ ፓፓያ ያሉ ፍራፍሬዎችን መመገብ።

በተጨማሪም ከሚመገቡት ምግብ ጋር ነጭ ሽንኩርት፣ ዝንጅብልና ቃሪያን ጨምሮ መመገብ እንዲሁም አበባ ጎመን፣ ሰላጣ እና ቆስጣ ያሉ አትክልቶችን ማዘውተርም የተሻለ መሆኑን ይገልጻሉ።

አኩሪ አተርና ነጭ ቦሎቄን ጨምሮ የጥራጥሬ ተዋፅዖዎችን መመገብ በሽታ የመከላከል አቅምን ለማጎልበት አስፈላጊ መሆኑንም ነው የገለጹት።

ስጋ ሳይበዛ፣ ለውዝ፣ የወተት ተዋፅዖ፣ እንቁላልና ጥቁር ቸኮሌት መመገብም በሽታ የመከላከል አቅምን ለማሳደግ እንደሚረዳም ገልጸዋል።

በቫይታሚን  ኢ የበለጸጉ ምግቦች

ቫይታሚን ኢን ከሱፍ፣ በቆሎና አትክልት ተዋፅዖዎች ማግኘት ይቻላል፤ እንዲሁም ፈሳሽ በብዛት መውሰድም አስፈላጊ መሆኑን ይመክራሉ።

ከአመጋገብ ባለፈም የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ ጠቀሜታ አለው፤ በሳምንት ከተቻለ ለስድስት ቀናት በቀን ለ30 ደቂቃ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ አስፈላጊ።

በተጨማሪም የግልና የአካባቢ ንጽህናን በመጠበቅ ራስን ከተላላፊ በሽታዎች መከላከልና መጠበቅ ይቻላል።

ምንጭ፦  healthline.com እና psychologytoday.com

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.