Fana: At a Speed of Life!

የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክ የቁም እስረኛ ሆኑ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክ ማንነታቸው ባልታወቁ ወታደራዊ ኃይሎች ዛሬ ማለዳ መኖሪያ ቤታቸው ተከብቦ የቤት ውስጥ እስረኛ እንደተደረጉ አል ሃዳድ የተባለ የቴሌቪዥን ጣቢያ ዘግቧል።

ሃምዶክ ላይ ይህ እርምጃ ከመወሰዱ በፊት የሱዳን ጦር የጠቅላይ አዛዥ የሚዲያ አማካሪና የሀገሪቱን ገዥ ሉዓላዊ ምክር ቤት አባል ጨምሮ በርካታ የሲቪል ባለስልጣናት በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገልጿል።
ባለፈው ወር ያልተሳካ የመፈንቅለ መንግስት ሴራ መደረጉን መንግስት ማሳወቁን ተከትሎ በወታደራዊው እና በሲቪል ቡድኖች መካከል መራር ቅራኔ ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገልጿል።
በካርቱም የኢንተርኔት አገልግሎት በዚህ ሰዓት የተቋረጠ በመሆኑ ምን እየተደረገ እንዳለ መረጃ ለማግኘት አዳጋች እንደሆነ ተገልጿል።
የመረጃ፣ የኢንዱስትሪ ሚኒስትሮችን ጨምሮ የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪና የሉዓላዊ ምክር ቤቱ ቃል አቀባይ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተጠቁሟል።
እስካሁን ድረስ በቁጥጥር ስር ከዋሉ ሚንስትሮች፣ የመንግስት ሀላፊዎች እና የፓርቲ መሪዎች መካከል ቀጥሎ የተጠቀሱት አሉበት ተብሏል፡፡
1. የመገናኛ ሚንስትር ሃሺም ሀሰበአልረሱል
2. የኢንዱስትሪ ሚንስትር ኢብራሂም አልሼክ
3. የማስታወቅያ ሚንስትር ሀምዛ በሉል
4. የሚንስትሮች የካቢኒ ጉዳዮች ሀላፊ ካሊድ ዩሱፍ
5. ሉዓላዊ የሽግግር ምክር-ቤት አመራር አባል መሀመድ አልፈኪ
6. የሱዳን ኮንግረስ ፓርቲ ሊቀመንበር ኡመር አደግበር
7. የአረብ ትንሳኦ ፓርቲ ሊቀመንበር አሊ አልረያህ አልሰንሁሪ
8. የካርቱም ከተማ ከንቲባ አይመን ኒሚር እና
9. የዲሞክራሲያዊ ለውጥ አብዮት ቃል-አቀባይ ጃፈር ሀሰን መሆናቸው ተገልጿል።
የሀሚቲ ጦር የካርቱም ከተማ አስፈላጊ ቦታዎችን እንዲጠብቅ ትዕዛዝ ተሰጥቶታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.