Fana: At a Speed of Life!

የሱዳን መንግስት በዳርፉር ከሚገኙ አማጽያን ጋር የሰላም ስምምነት ተፈራረመ

አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 25፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) የሱዳን መንግስት እና በዳርፉር የሚገኘው ዋነኛው አማጺ ቡድን ጋር የሰላም ስምምነት ላይ መድረሳቸው ተገለፀ።

ስምምነቱ በመካከላቸው ለ17 ዓመታት የዘለቀውን የግጭት ምዕራፍ ይቋጫል ተብሏል፡፡

ስምምነቱን ለረጅም ጊዜ ለድርድሩ ድጋፍ ስታደርግ በቆየችው በደቡብ ሱዳን ጁባ ተከናውኗል፡፡

በትናትናው ዕለት ወደ ጁባ ያቀኑት የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክ ስምምነቱ ጊዜ መውሰዱን ጠቅሰዋል፡፡

በሀገሪቱ የሚገኙ የሶስቱን አማጽያን ጥምረት በመወከል ማሊክ አጋር ስምምነቱን መፈረማቸው ተነግሯል፡፡

በሂደቱ በጸጥታ፣ በመሬት ባለቤትነት፣ በፍትሕ፣ በስልጣን ክፍፍል እንዲሁም በጦርነት ምክንያት ከቀያቸው  በተፈናቀሉ ሰዎች ዙሪያ ስምምነት ደርሷል፡፡

በተጨማሪም የአማጺያን ወታደሮች ትጥቅ በመፍታት በብሔራዊ የሀገሪቱ ጦር ውስጥ እንዲካተቱ የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡

ምንጭ፦ አልጀዚራ

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.