Fana: At a Speed of Life!

የሱዳን መከላከያ ሚኒስትር ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 16፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ)የሱዳን መከላከያ ሚኒስትር ሌተናል ጄኔራል ጃማል ኢል ዲን ኦዑር ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።
 
በሱዳን መንግስት እና በሀገሪቱ አማፂያን መካከል በደቡብ ሱዳን እየተካሄደ በሚገኘው ድርድር ለመሳተፉ ጁባ ባቀነቡት ነው ህይወታቸው ያለፈው።
 
ሌተናል ጄኔራል ጃማል ኢል ዲን ኦማር ሀሰን አልበሽር ከስልጣን ከወረዱ በኋላ ሀገሪቱን እየመራ የነበረው የወታደራዊ ምክር ቤት አባል ነበሩ።
 
የመከላከያ ሚኒስትሩ ከልብ በሽታ ጋር በተያያዘ ህይወታቸው ማለፉን ነው የሱዳን መንግስትና ወታደራዊ ባለስልጣናት ያስታወቁት።
 
ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክም በመከላከያ ሚኒስትሩ ህልፈት የተሰማቸውን ሀዘን ገልፀዋል።
 
ምንጭ፦ ሬውተርስ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.