Fana: At a Speed of Life!

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ሰራተኞች የዘማች ቤተሰቦችን ሰብል ሰበሰቡ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 20 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ሰራተኞች በኦሮሚያ ክልል ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን የበቾ ወረዳ ዘማች ቤተሰቦችን ሰብል ሰበሰቡ፡፡
 
በወረዳው በሶዮማ ቀበሌ በመገኘት የዘማች ቤተሰቦችን ሰብል በመሰብሰብ፤ አለኝታነታቸውን ያሳዩ ሲሆን በቀጣይም እገዛ እንደሚያደርጉ አረጋግጠዋል።
 
የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጂማ ዲልቦ “አሸባሪው ህወሓት በኢትዮጵያ ላይ የደቀነውን የህልውና አደጋ ለመቀልበስ ሁሉም በሚችለው አቅም መረባረብ አለበት” ብለዋል፡፡
 
የአገር መከላከያ ሰራዊት እና ሌሎች የፀጥታ አካላት የኢትዮጵያን አንድነት ለማረጋገጥ የህይወት መስዋዕትነት እየከፈሉ እንደሆነ ጠቅሰው፤ “እኛም በቻልነው ሁሉ ከጎናቸው መሆን አለብን” ሲሉ ተናግረዋል፡፡
 
“ከሰራዊቱ ጎን ከመሰለፍ ባለፈ ደጀን በመሆን የዘማች ቤተሰቦችን መደገፍና ማገዝ ይኖርብናል”ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
 
የሲቪል ማህበራትም ተፈናቃዮችን በመደገፍ እና መልሶ በማቋቋም ላይ በስፋት ሊሰሩ እንደሚገባ አመልክተዋል፡፡
 
ለኢዜአ አስተያየታቸውን የሰጡ የድርጅቱ ሰራተኞችም የአገሪቱን ህልውና ለማስቀጠል የቻሉትን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.