Fana: At a Speed of Life!

የሲዳማ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ በመወያየት ውሳኔ አሳለፈ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ክልል መስተደድር ምክር ቤት በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ በመወያየት ውሳኔ አሳልፏል፡፡

የክልሉ መስተዳደር ምክር ቤት በትናንትናው ዕለት በጀመረው ሰብሰባው በሶስት አጀንዳዎች ላይ የተወያየ ሲሆን÷ በዛሬው ዕለትም በማፅደቅ ተጠናቋል።

በዚህም የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የመንግሥት ሠራተኞች አዋጅ እና የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ከተሞችን እንደገና ለማቋቋምና ለማደራጀት፣ ሥልጣንና ተግባራቸውን ለመወሰን የወጣ አዋጅ ላይ የመስተዳድር ምክርቤቱ በጥልቀት ከተወያየ በኃላ መስተካከል ያለባቸው አስፈላጊ ማስተካከያ ተደርጎ ለክልሉ ምክርቤት ቀርቦ እንዲፀድቅ ውሳኔ አሳልፏል፡፡

በተጨማሪም በቀረበው ለኢንቨስትመንት ተግባር የሚውል የገጠር መሬትን በሚመለከት ረቂቅ ደንብ ላይ በዝርዝር ከተወያየ በኋላ ሥራ ላይ እንዲውል በሙሉ ድምፅ ማፅደቁን ከሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.