Fana: At a Speed of Life!

የሲዳማ ክልል መንግስት ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ሲያካሂዱት የነበረው የምክክር መድረክ ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ክልል መንግስት ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ በድህረ ጦርነት መዛነፎች እና እርምቶች ላይ ሀዋሳ ከተማ ላይ ሲያካሂዱት የነበረው የምክክር መድረክ ተጠናቀቀ፡፡

የሲዳማ ክልል መንግስት ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ የድህረ ጦርነት መዛነፎች እና እርምቶች በሚል በተዘጋጀ ሀገራዊ ሰነድ ላይ በጥልቀት ምክክር ሲያደርግ የነበረውን መድረክ የተለያዩ ሀገራዊና ክልላዊ ነባራዊ ሁኔታዋችን በጥልቀት በመፈተሽና በመወያየት ማጠናቀቁ ተገልጿል፡፡

መድረኩን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ እና የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አብርሃም ማርሻሎ መርተውታል።

በውይይት መድረኩ ላይ አቶ ደስታ ሌዳሞ እንደገለፁት ፥ በህብረ ብሔራዊ ዘመቻ የተመዘገቡ ድሎች መላው ኢትዮጵያዊያን በጋራ ሆነው ሀገራቸውን ከሚገዳደርና ከሚዋጋ ባንዳ በማዳን ክብሯንና ልእልናዋን ለማረጋገጥ በከፈሉት የህይወትና የአካል መስዋዕትነት የተገኘ ታሪካዊ ድል ነው ፤ የሀገራቸው የፍቅር ስሜት ያደረባቸው በውጭና በሀገር ውስጥ ያሉ ኢትዮጵያውያን የፈጠሩት ሀገራዊ አንድነትና ኢትዮጵያዊነት መንፈስ በቀጣይ ተልዕኮዎችና ተግባሮችም በተደራጀና በተጠናከረ መንገድ እንዲቀጥሉ በአንክሮ ሊሰራ እንደሚገባ ገልጸዋል።

የክልሉ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች በዚሁ መድረክ በዝርዝር ወቅታዊ አገራዊና ክልላዊ ጉዳዮች ዙሪያ ያደረጉት ምክክር በከተሞች፣ በወረዳዎች እና ቀበሌዎች ህዝቡ ምክክር እንደሚያደርግ ከክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.