Fana: At a Speed of Life!

የሲዳማ ክልል ምክር ቤት ለ2013 ዓ.ም 10 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር በጀት አፀደቀ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ክልል ምክር ቤት የ2013 ዓ.ም የክልሉ በጀት 10 ቢሊየን 725 ሚሊየን 142 ሺህ ብር እንዲሆን የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ በሙሉ ድምፅ አፅድቆታል።
የሲዳማ ክልል ምክር ቤት ከትናንትናው ዕለት ጀምሮ 1ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባኤውን በሀዋሳ ከተማ አካሂዷል።
በቅርቡ በሀገሪቱ 10ኛ ክልል በመሆን የተዋቀረው የሲዳማ ክልል ምክር ቤት የመጀመሪያ ጉባኤውን ነው ያካሄደው።
ምክር ቤቱ ዛሬ በተጠናቀቀው ጉባኤውም የጠቅላይ ፍርድ ቤት እና በዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት የ2013 ዕቅድ ዙሪያ የመከረ ሲሆን በተለያዩ አዋጆች እና ሹመቶች ላይም ውሳኔ አሳልፏል።
በዚህም የሲዳማ ክልል ምክር ቤት አንደኛ ዓመት አንደኛ መደበኛ ጉባኤ ከወረዳ እስከ ክልል ማዕከል ባሉ ፍርድ ቤቶች የሚያገለግሉ የ24 ዳኞችን ሹመት በማጽደቅ ተጠናቋል።
በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ደምሴ ዱላቻ አቅራቢነት በምክር ቤቱ የተሾሙት 24 ዳኞች ከክልል እስከ ወረዳ ባሉ ፍርድ ቤቶች የሚያገለግሉ መሆናቸው ተገልጿል።
በምክር ቤቱ ከተሾሙ 24 ዳኞች መካከል ሁለቱ ሴቶች መሆናቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።
122,240
People Reached
5,172
Engagements
Boost Unavailable
1.6K
62 Comments
69 Shares
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.