Fana: At a Speed of Life!

የሳንባ ምች ለህፃናት ሞት ቀዳሚ መንስኤ መሆኑ ተገለጸ

 

አዲስ አበባ፣ ህዳር 13፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) “የአየር ብክለትን በመቀነስ፣ መሰረታዊ የጤና እና የስርዓተ ምግብ አገልግሎቶች ጥራትን በማሻሻል በሳምባ ምች የሚሞቱ ህፃናትን እናትርፍ” በሚል መሪ ቃል የዓለም የሳንባ ምች ቀን በጅግጅጋ ከተማ ተከብሯል።

የሶማሌ ክልል ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ መሃሙድ መሃመድ አብዲ÷ ከሳንባ ምች በሽታ ጋር ተያይዞ ይደርሱ የነበሩ ችግሮች ላይ መሻሻሎች መኖራቸውን ተናግረዋል።

ከ5 ዓመት እድሜ በታች የሚከሰተውን ሞት በመቀነስ ስትራቴጂክ ግብን ለማሳካት ሁሉም አጋር ድርጅቶች እያደረጉት ያለውን ጥረትና ድጋፍ እንዲያጠናክሩም ጥሪ አቅርበዋል።

በጤና ሚኒስቴር የእናቶችና ህፃናት ጤና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶክተር መሰረት ዘላለም በኢትዮጵያ በአመት 36 ሺህ የሚሆኑ ህጻናት እድሜያቸው 5 አመት ሳይሞላ በዚሁ በሽታ እንደሚሞቱ አስረድተዋል።

ባለፉት አመታት የህፃናትን ሞት ለመከላከል በተደረገው ጥረት በፈረንጆቹ 2005 በህይወት ከሚወለዱት 1 ሺህ ህፃናት ውስጥ 123 የሚሆኑት ይሞቱ የነበረውን፥ በ2019 ወደ 59 ዝቅ ማድረግ መቻሉን ገልጸዋል።

1 ሺህ በህይወት ከሚወለዱት ህጻናት ከ5 አመት በታች የሞት ምጣኔ ሲታይ ከፍተኛው በሶማሌ ክልል 101 እና ዝቅተኛው በአዲስ አበባ 26 እንደሆነ መገለጹን ከጤና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.