Fana: At a Speed of Life!

የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን የምክክር መድረክ በኦስትሪያ በመካሄድ ላይ ነው

አዲስ አበባ ፣ ጥር 25፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ሚና ለዘላቂ የልማት ግቦች በሚል የምክክር መድረክ በኦስትሪያ ቬና ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

የምክክር መድረኩ ለዘላቂ የልማት ግቦች መሳካት የአባል ሀገራት ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ነባራዊ ሁኔታ ላይ በጥልቀት ለመወያየት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የተዘጋጀ  ነው።

እንዲሁም በሀገር በቀል እውቀት እና በማደግ ላይ ያሉ ቴክኖሎጂ ጠቀሜታና ተግዳሮቶች ዙሪያ ተወያይቶ የፖሊሲ አቅጣጫዎችን ለማስቀመጥ እና የአባል ሀገራት አቅም ግንባታ ፍላጎትን በመለየት የተጠናከረ ድጋፍ ለማድረግ ያለመም ነው።

በምክክር መድረኩ በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የሳይንስና ምርምር ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄኔራል ዶክተር ሰለሞን ቢኖርን ጨምሮ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት፣ አውሮፓ ህብረት አባላት እና ከ30 ሀገራት የተወከሉ ተጋባዥ የመንግስት ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

የምክክር መድረኩ ለቀጣይ ሁለት ቀናት እንደሚቀጥልም ከሣይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.