Fana: At a Speed of Life!

የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የከተማ አስተዳደሩ ትኩረት ሰጥቶ ይሰራል- ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 17፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የከተማ አስተዳደሩ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ አስታወቁ።

የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ከተለያዩ ክፍለ ከተሞች ከተውጣጡ ሴቶች ጋር ውይይት አካሂደዋል፡፡

ከተማዋ በጀመረችው የልማትና የለውጥ ጎዳና ወደፊት እንድትገሰግስ የሴቶች ተሳትፎ ከምንጊዜውም በላይ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ወይዘሮ አዳነች አቤቤ እንደገለጹት ተናግረዋል፡፡

በሴቶች እና ህጻናት ላይ የሚደርሰውን ጥቃት አስቀድሞ በመከላከል እና ጥቃት አድራሾችን ለፍርድ በማቅረብ ረገድ የከተማ አስተዳደሩ እንደሚሰራም ገልጸዋል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እና ከተሰብሳቢዎቹ የተነሱ ጥያቄዎችን ሁሉ መፍትሄ እንዲያገኙ ቅድሚያ ሰጥቶ እንደሚሰራ መናገራቸውን ከአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በዝግጅቱ ላይ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤን ፣ የሴቶች ህፃናት ወጣቶች ሚኒስትር ወ/ሮ ፊልሰን አብዱላሂ ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ወ/ሮ አበበች ነጋሽ ከሌሎች ሴት አመራሮች ጋር በመሆን የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ለመከላከል “ምክንያት አልሆንም” በሚል መሪ ቃል የአፍ መሸፈኛ ጭምብል የማድረግ ንቅናቄ አስጀምረዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.