Fana: At a Speed of Life!

“የሴቶች ተሣትፎና ተጠቃሚነት ለሁለንተናዊ ብልጽግና” በሚል መሪ ቃል በጋምቤላ የሴቶች የምክክር መድረክ ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 24 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) “የሴቶች ተሣትፎና ተጠቃሚነት ለሁለንተናዊ ብልጽግና” በሚል መሪ ቃል በጋምቤላ ብልጽግና ፓርቲ የተዘጋጀ የሴቶች የምክክር መድረክ ተካሄደ፡፡

የክልሉ ርዕሠ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ ዜጎች በህገ-መንግስቱ የተቀመጠላቸውን መብት በመጠቀም በሁሉም መስኮች የተመዘገቡ ለውጦችን አስጠብቆ ለማቆየትና የዛሬውንና የመጭውን ትውልድ ጥቅምና ፍላጎት በዘላቂነት ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሠራ ነው ብለዋል፡፡

በ”መደመር ” እሳቤ ላይ የተመሠረተውን ሁለንተናዊ የለውጥ እንቅስቃሴ ዘላቂና አስተማማኝ በማድረግ ሃገሪቱ በብልጽግና ጎዳና ላይ የጀመረችው ግስጋሴ ተጠናክሮ መቀጠሉን አስታውቀዋል።

አያይዘውም የበለፀገች ህብረ-ብሔራዊ ሃገር በመገንባት ሂደት ተፅዕኖ ፈጣሪ ሴቶችን ለመፍጠር የሴት የአደረጃጀቶችን ማጠናከር ወሳኝ መሆኑንም ተናግረዋል ።

በምክትል ርዕሠ መስተዳድር ማዕረግ የጋምቤላ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ላክዴር ላክባክ፥ የሴቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የብልጽግና ፓርቲና መንግስት ፖሊሲና ስትራቴጂ እንዲሁም የረጅም ጊዜ ዕቅድ ነድፎ ተግባራዊ በማድረግ ላይ መሆኑን ተናግረዋል ።

ሴቶች ላይ የሚደረስወን ፆታዊ አድሎ ለመከላከል በሚደረገው ትግል ግንባር ቀደም ተዋናይ በመሆን በአካባቢያቸው በሚደረጉ የልማት እንቅስቃሴዎች ላይ እንዲሳተፉ ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝም አመላክተዋል፡፡

በሃገሪቱ በሚደረጉ ምርጫዎች ሴቶች በመምረጥም ሆነ በመመረጥ ተሳታፊነታቸው እየጨመረ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ ዘንድሮ በሚካሄደው ሃገራዊ ምርጫ ድርሻቸው 50 በመቶ መደረጉንም ጠቅሰዋል፡፡

ምርጫው ፍትሃዊ፣ ሠላማዊና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ሴቶች የበኩላቸውን ኃላፊነት መወጣት እንደሚጠበቅባቸውም አስገንዝበዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.