Fana: At a Speed of Life!

የሴቶች የኢኮኖሚ ብቃት ፎረም በብሔራዊ ደረጃ ተቋቋመ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)የሴቶችን የኢኮኖሚ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማሳደግ በተቀናጀ መልኩ ለመስራት የሚያስችል የሴቶች የኢኮኖሚ ብቃት ፎረም ዛሬ በብሔራዊ ደረጃ ተቋቁሟል፡፡

በፎረሙ መመስረቻ መርሃ ግብር የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ አለሚቱ ኦሞድ ÷ፎረሙ ሴቶች በኢኮኖሚው ዘርፍ ተጠቃሚ እንዳይሆኑ መሰናክል የሆኑባቸውን ችግሮች በጥናት በመለየት የመፍትሄ አቅጣጫ ለማስቀመጥ፣ የሴቶችን የእርስ በእርስ ግንኙነት ለማጠናከርና በሴቶች መካከል የሚደረገው የልምድ ልውውጥ የሀብት ብክነትንና የስራ ድግግሞሽ ለማስቀረት የሚያግዝ ነው ብለዋል፡፡

የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ንጉሱ ጥላሁን በበኩላቸው÷ በኢኮኖሚ እራስን መቻል በሁሉ ነገር ብቃትን ያላብሳል ያሉ ሲሆን ÷ሴቶች በኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ብቻ ሳይሆን ተሳትፎአቸው ሲረጋገጥ የውሳኔ ሰጪነታቸው ማህበራዊ ተሳትፎአቸውና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴያቸው ሊረጋገጥ እንደሚችል ገልጸዋል፡፡

ፎረሙን መንግስታዊና መንግስታዊ ያሆኑ ድርጅቶች የንግድ ዘርፍና የፋይናንስ ሴክተሩን በአባልነት እንደሚያቅፍ ከሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.