Fana: At a Speed of Life!

የሴቶች ፣ህጻናትና ወጣቶች ሚኒስቴርና የአመራር አባላት የአንድ ወር ደሞዛቸውን ለገበታ ለሀገር ፕሮጀክት ትግበራ እንዲዉል ወሰኑ

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 17 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ)የሴቶች ፣ህጻናትና ወጣቶች ሚኒስቴርና የአመራር አባላት የአንድ ወር ደሞዛቸውን ለገበታ ለሀገር ፕሮጀክት ትግበራ እንዲዉል መወሰናቸውን የሴቶች፣ህጻናትና ወጣቶች ሚኒስትር ወይዘሮ ፊልሰን አብዱላሂ አስታወቁ፡፡

ሚኒስትሯ እንደገለፁት ÷ታላላቅ ፕሮጀክቶች በቀጥታ ከሚሰጡት አገልግሎት ባሻገር ሁላችንንም እርስበርስ በማስተሳስር ለሀገራችን ህዝቦች ብሔራዊ መግባባትንና የይቻላል መንፈስን ፣ለሀገራችን ክብረ ፣ ለሀገራችን ሴቶች፣ህጻናትና ወጣቶች የብልጽግና ተስፋን የሚያጎናጽፍ፣ለአመራሩ ሞራልና ለላቀ ሃሳብ የሚያነሳሱ ናቸው፡፡

ይህም ትሩፋት ለሴቶች፣ህጻናትና ወጣቶች የላቀ እንደሆነ በመንገዘብ የሴቶች ፣ህጻናትና ወጣቶች ሚኒስቴርና የአመራር አባላት የአንድ ወር ደሞዛቸንን ለገበታ ሀገር ፕሮጀክት ትግበራ እንዲዉል ወስነናል ብለዋል፡፡

ይህ ፕሮጀክት በሴቶችና ወጣቶች ተሳትፎና ስራ ፈጠራ ታጅቦ ኢኮኖሚውን እንደሚደግፉ አዎንታዊ ተስፋ አለን ያሉት ሚኒስትሯ÷ ህፃናቶች ከዚህ የተሻለ ስራ መስራት እንዲቻል በቻልነው ሁሉ ለመደገፍ ቃል እንገነባለን ብለዋል፡፡

በዚሁ አጋጣሚ ለፕሮጀክቱ ስኬት በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደር ያሉ የዘርፉ አደረጃጀቶች፣ ሲቪክ ማህበራት፣ ሴቶችና ወጣቶች የሚቻላቸዉን ሁሉ እንዲያበርክቱ ሚኒስትሯ ጥሪ ማስተላለፋቸውን ከየሴቶች፤ህጻናትና ወጣቶች ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ መላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.