Fana: At a Speed of Life!

የሴካፋ ውድድር በባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ሊካሄድ ነው

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 18 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ 23 ዓመት በታች የምስራቅና መካከለኛ አፍሪካ ዋንጫ ውድድር በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት በባህር ዳር ከተማ ይካሄዳል፡፡
ጨዋታው ከሰኔ 26 እስከ ሀምሌ 11 ቀን 2013 ዓ.ም የሚካሄድ ሲሆን 11 የምስራቅና መካከለኛ አፍሪካ ሀገሮች እና አንድ ተጋባዥ ሀገር በድምሩ 12 አገሮች የሚካፈሉበትን አህጉር አቀፍ ጨዋታ መሆኑ ተገልጿል፡፡
የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድንም ቅድመ ዝግጅቱን አጠናቆ በትናንትናው እለት ባህርዳር ከተማ ገብቷል፡፡
በውድድሩ የሚሳተፉ የምሥራቅና መካከለኛው ቀጠና የአፍሪካ ሀገራት ብሔራዊ ቡድኖችም በቅርብ ቀናት ባሕር ዳር ከተማ እንደሚገቡ መገለፁን ከአማራ ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.